የባንክ ሂሳብን ከፋይዳ (ብሔራዊ መታወቂያ) ጋር የማስተሳሰር እስከ ሰኔ 30 ድረስ ተራዘመ

- Advertisement -
Sidebar AD

በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ ከተሞች ደግሞ እስከ ግንቦት 6 ብቻ ነው ተብሏል።

#Ethiopia | የባንክ ሂሳቦችን ከፋይዳ ቁጥር ጋር የማስተሳሰር ስራ ከታህሳስ 15 ቀን 2018 ዓ.ም (እ.ኤ.አ ዲሴምበር 24) ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ባንኮች ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወቃል።

የማስተሳሰሩ ሥራ እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም የተከናወነ ቢሆንም አሁንም በርካታ ደንበኞች ሂሳባቸውን ከፋይዳ ቁጥራቸው ጋር ባለማስተሳሰራቸው ምክንያት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚከተሉትን ውሳኔዎች አሳልፏል።

1. በሀረር፣ አዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ አስተዳደር፣ ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ደብረብርሃን፣ ኮምቦልቻ፣ ሀዋሳ፣ አርባ ምንጭ፣ ወላይታ ሶዶ፣ ሆሳዕና፣ ወራቤ፣ ቡታጂራ፣ ወልቂጤ፣ ሸገር፣ ጅማ፣ አዳማ፣ ሻሸመኔ፣ ቢሾፍቱ፣ ባቱ፣ አምቦ፣ መቐለ፣ አክሱም፣ ዓዲግራት፣ ጋምቤላ እና አሶሳ ከተሞች የሚገኙ ደንበኞች እስከ ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም (May 14, 2026) ድረስ ሂሳባቸውን ከፋይዳ ቁጥር (ብሔራዊ መታወቂያ) ጋር ማስተሳሰር እና ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።

2. በተቀሩት የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚገኙ የባንክ ቅርንጫፍ ደንበኞች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም (July 07, 2026) ድረስ ማጠናቀቅ ይኖርባቸዋል።

3. በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሂሳባቸውን የማያስተሳስሩ ደንበኞች የባንክ ሂሳባቸው ከወጪ ወይም ተቀናሽ ግብይት የታገደ (No Debit) እንደሚታገድና እገዳው የሚነሳው ደንበኛው የፋይዳ መታወቂያ ቁጥሩን ከባንክ ሂሳብ ቁጥሩ ጋር ሲያስተሳስር ብቻ እንደሚሆን ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

4. ከዚህ በላይ የተሰጠው አቅጣጫ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብን እና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ነዋሪዎችን አይመለከትም። በውጭ ሀገር የሚገኙ የሂሳብ ባለቤቶች አስፈላጊውን ማስረጃ በአካል ወይም በህጋዊ ወኪሎቻቸው አማካኝነት ለባንኮች በማቅረብና በማረጋገጥ ከዚህ ውሳኔ ነፃ መሆን ይችላሉ ሲል ባንኩ መልዕክቱን አስተላልፏል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2