በህገ ወጦች ተይዘናል በማለት ቤተሰቦቻቸው 3መቶ ሺ ብር እንዲልኩላቸው የጠየቁ ታዳጊዎች ከአነ ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር …

- Advertisement -
Sidebar AD
በህገ ወጦች ተይዘናል በማለት ቤተሰቦቻቸው 3መቶ ሺ ብር እንዲልኩላቸው የጠየቁ ታዳጊዎች ከአነ ግብረ አበሮቻቸው በቁጥጥር ስር ዋሉ።
***
አዲስ አበባ- ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተጠርጣሪዎች የወንጀል ድርጊቱን የፈፀሙት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው የካ አባዶ አካባቢ ነው፡፡ የ15 እና የ16 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሴት ታዳጊዎቹ ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ለትምህርት ብለው እንደወጡ ሳይመለሱ ይቀራሉ፡፡
በልጆቹ መጥፋት ቤተሰቦቻቸው ተጨንቀው በነበሩበት ወቅት ታዳጊዎቹ ስልክ በመደወል 3መቶ ሺህ ብር እንዲላክላቸው ነገር ግን ገንዘቡ ካልተላከላቸው የያዟቸው ግለሰቦች ጉዳት ሊያደርሱባቸው መሆኑን ይገልፃሉ፡፡
የወንጀሉ ጉዳይ ሪፖርት የደረሰው የለሚ ኩራ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ባደረገው ክትትል እና ፍለጋ ሚያዝያ 13 ቀን 2018 ዓ/ም ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ታዳጊዎቹን ከሁለት ወንዶች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታውቋል፡፡
ፖሊስ ባደረገው ምርመራ ታዳጊዎቹ ከሁለት ወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ እንደነበር ያረጋገጠ ሲሆን አራቱን ታዳጊዎች እና ለታዳጊዎቹ የመኝታ ክፍል ያከራየን ግለሰብ ይዞ ምርመራው መቀጠሉን ገልጿል፡፡
ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ አስበው እና ተነጋግረው ድርጊቱን አቀነባብረው እንደፈፀሙት ታዳጊዎቹ ለፖሊስ ከሰጡት ቃል መረዳት ተችሏል፡፡
ሆቴል ቤቶች ሆኑ የመኝታ ክፍል የሚያከራዩ ተቋማት ለህፃናት ሆነ ለታዳጊዎች የመኝታ ክፍል ማከራየትና አልኮል መጠጥ መሸጥ እንደሌለባቸው ፖሊስ አሳስቦ ቤተሰብም ልጆቻቸው የት እና ከእነ ማን ጋር እንደሚውሉ የማረጋገጥ ልምድ ሊያደብር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: