ባሕር ዳር ላይ ሰው ገድሎ የተሰወረው ተጠርጣሪ መቐለ ላይ በትግራይ ክልል ፖሊስ ተያዘ።

- Advertisement -
Sidebar AD

በባሕርዳር ከተማ ማህሌት ማሩ የተባለችን እንስት ” የአድማ ብተና ” አባል በሆነው ተጠርጣሪ ያምራል አለበል አለሙ ” ተደፍራ እና ተገድላ ተገኘች ” የሚል መረጃ ሲሰራጭ ነበር።

የግድያ ጥቃቱ የደረሰበትን ሁኔታ በተመለከተ፣ ከስፍራው የወጣውና በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨው አብዛኛው መረጃ፣ ተጠርጣሪው እንስቷ ከምትሰራበት ሆቴል እየተስተናገደ አምሽቶ ” አስገድዶ ወደ ሌላ ሆቴል በመውሰድ ከደፈራት በኋላ ገደላት ” የሚል ነው።

የወንጀል ድርጊቱ ብዙዎችን ያቆጣ ነው።

የወንጀል ድርጊቱን በመፈጸም የተጠረጠረው ግለሰብ ድርጊቱን ፈጽሞ ከአካባቢው ተሰውሮ ነበር።

ምንም እንኳን የአማራ ክልል ፖሊስ ስለ ግድያው ዝርዝር መረጃ ይፋ ባያደርግም ህዝቡ ያለበትን እንዲጦቅም ጥሪ አቅርቦ ፍለጋ ሲያካሂድ ነበር።

ዛሬ የአማራ ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ በነፍስ ግድያ ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈለግ የነበረው ያምራል አለበል አለሙ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ፖሊስ ” ያምራል አለበል አለሙ የተባለው ተጠርጣሪ ግድያ ፈጽሞ ከአካባቢው በመሰወር ለረጅም ጊዜ ሲፈለግ ቆይቷል ” ብሏል።

ለመያዝ ክትትል ሲደረግ ቆይቶ በትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ተሸሽጎ እንደሚገኝ በመረጋገጡ በተደረገ የተቀናጀ ስራ በቁጥጥር ስር ሊውል እንደቻለ አማራ ፖሊስ ገልጿል።

የአማራ ክልል ፖሊስ፣ የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

በሌላ በኩል ቲክቫህ ኢትዮጵያ እንስቷ በምን ሁኔታ ግድያ እንደተፈጸመባት አንድ የአማራ ክልል ፖሊስ አካልን ጠይቆ ” ምርመራ ላይ ስለሆነ የሚገልጹት ምርመራ የሚሰሩት ናቸው ” ብለዋል።

እስካሁን ባለው ክትትል ስለእንስቷ አሟሟት የተገኘ መረጃ ካለ በድጋሚ እንዲገልጹ ስንጠይቃቸውም፣ ” ገና ምርመራ ላይ ያለ ጉዳይ ነው ” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

@tikvahethiopia




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2