“ታፍነናል” በማለት 300 ሺህ ብር ከቤተሰቦቻቸው የጠየቁት ታዳጊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በከተማችን አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ (የካ አባዶ) የሚኖሩ የ15 እና የ16 ዓመት ሴት ታዳጊዎች፣ ለስደት መሄጃ ገንዘብ ፍለጋ ሲሉ የፈጠሩት “የታፈንን” ድራማ በፖሊስ ክትትል ከሸፈ።

​ የክስተቱ ዝርዝር፦

ሚያዝያ 12 ቀን 2018 ዓ/ም ለትምህርት የወጡት ታዳጊዎች ሳይመለሱ ቀርተው፣ “300 ሺህ ብር ካልተላከ ገዳዮቹ ጉዳት ሊያደርሱብን ነው” በማለት ቤተሰቦቻቸውን አስጨንቀዋል።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል ታዳጊዎቹ ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ከሁለት ወንድ ጓደኞቻቸው ጋር ሲዝናኑ ተገኝተዋል። አራቱም ታዳጊዎችና የመኝታ ክፍል ያከራያቸው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ታዳጊዎቹ ወደ ውጭ ሀገር ለመሄድ አስበው ገንዘብ ለማግኘት ድርጊቱን እንዳቀነባበሩት ለፖሊስ ቃል ሰጥተዋል።

ልጆቻችሁ የት እንደሚውሉ፣ ከማን ጋር እንደሚውሉና ምን እያቀዱ እንደሆነ የመከታተል ልምድ ሊኖራችሁ ይገባል።

​ ሆቴሎችና የመኝታ ቤቶች ለታዳጊዎች አልኮል ከመሸጥና ክፍል ከማከራየት እንዲቆጠቡ ፖሊስ ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥቷል።

​ልጆቻችንን እንከታተል፤ ከስደትና ከጥፋት እንታደጋቸው!

​#getu #AddisAbabaPolice #LemiKura #TeenageCrime #SafetyFirst #EthiopianFamily #Awareness #SocialIssue #አዲስአበባፖሊስ #ለሚኩራ #የልጆችጥበቃ #ማስጠንቀቂያ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: