የሊባኖስ ፕሬዚዳንት ጆሴፍ አውን አገራቸው ከእስራኤል ጋር የጀመረችውን የአስር ቀን “የተኩስ አቁም ስምምነት የጊዜ ገደብ ለማራዘም” ንግግር እየተደረገ መሆኑን ገለፁ።
ሊባኖስ እና እስራኤል ሐሙስ ዕለት በዋሺንግተን ተገናኝተው ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል። በሁለቱ አገራት መካከል የአስር ቀን የተኩስ አቁም ስምምነት የተደረሰው ባለፈው ሳምንት ነበር።
አውን በኤክስ ገጻቸው ላይ ውይይቶቹ የተዘጋጁት “የእስራኤል ጥቃት ሙሉ በሙሉ በሚቆምበት፣ እስራኤል ከሊባኖስ ግዛቶች ለቅቃ በምትወጣበት፣ እስረኞችን በመመለስ፣ በዓለም አቀፍ ድንበሮች አካባቢ ወታደሮች በማሰማራት እና በጦርነቱ የወደሙትን መልሶ በመገንባት ላይ ነው።”
አውን የሊባኖስ አቋምን ሲናገሩ “የምንደራደርበት ግልጽ ነው፤ ከሊባኖስን ሉዓላዊነት እና ጥቅም በስተቀር ምንም ዓይነት ስምምነት፣ ድርድር፣ እጅ መስጠት አይኖርም” ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ በዚሁ ልጥፋቸው ላይ ከአሜሪካ የተገኘው ድጋፍ ለሊባኖስ “ማባከን የሌለብንን ዕድል” ፈጥሮልናል ብለዋል።









No comments yet.