የቅድስት አርሴማ ረድኤት እና ምልጃዋ አይለየን

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ራሷን የክርስቶስ ሙሽራ አድርጋ የለየች የፊቷ መልክ እጅግ ልዩ፣ ደምግባቷ ያማረ ነበረች።

ራሷን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽርነት ያጨችና ዓለምን የናቀች፣ ለመንፈሳዊ ሕይወቷ ፍጹም ራሷን አሳልፋ የሰጠችም ናት፡፡ ውብ ሚስት እንዲፈልጉለት መልእክተኞቹን የላከው ከሀዲው ንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ ሮሜ ውስጥ ባለ አንድ ገዳም ውስጥ ከሌሎች ደናግል ጋር ያገኟትን ቅድስት አርሴማ ሥዕል እንዳየ እጅግ ወደዳትና አምጡልኝ አለ፡፡ እርሷ ግን ከገዳሙ እመምኔትና ከሌሎቹ ደናግላን ጋር ወደ አርማንያ ሸሸች። አካባቢውን የሚገዛው ንጉሥ ድርጣድስ ከንጉሡ ዲዮቅልጥያኖስ መልእክት ደርሶት ሲያስፈልጋት ከደናግሉ ጋራ አገኛት። እርሱም በውበቷ በእጅጉ ተስቦ ለራሱ ሊያደርጋት ወስኖ ከደናግሉም ጋራ ካሠራት በኋላ እናታችን ቅድስት አርሴማን ሊያታልላት ይጥር ጀመር።

አልሆን ሲለውም እመምኔቷን እንድታባብላት ቢልካትም እርሷ ግን እንዲህ ላለው ምድራዊ ኃላፊ ነገር እንዳትታለይ፤ ሰማያዊ ሙሽርነትሽንና ንጽሕናሽን አጽኚ” ብላ ይበልጥ አጸናቻት። ንጉሡም ቅድስት አርሴማን በግድ ይዟት ሊሄድ ሲል ኃይለ መንፈስ ቅዱስ አድሮባታልና ያንን በጦር የጎለመሰ ሰውነት ያለው ንጉስ ከመሬት ፈጠፈጠችው። አንዲት ትንሽ ወጣት እንደምን ጣለችኝ ብሎ እጅግ በማፈሩም እጅግ ተቆጥቶ ሥቃይዋን ሊያበዛባት ተነሳ በደናግሉ ሁሉ ፊትም አሠራትና እንድትሳቀቅ በፊቷ አንድ በአንድ አንገታቸውን ቀላቸው። እርሷ ግን ቅዱሳኑ ሰማያዊ አክሊልን ሲቀበሉ ትመለከት “አይዟችሁ!” እያለችም ታጽናናቸው ነበር። ይህን ሲጨርስም “አንቺን እንደሌሎቹ ቶሎ አልገድልሽም” ብሎ በብዙ መከራ እጅግ አሠቃያት። ሁለቱን ጡቶቿን ቆረጠ፤ ሁለት ዐይኖቿንም አወጣቸው፡፡ ንጽሕት ድንግል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ልዩ የብርሃን ዐይኖችን ሰጠቻት። በመጨረሻም ከቀሩት ሰባ አምስት ወንዶችና ሃያ ሰባት ደናግል ሴቶች ጋራ መስከረም ሃያ ዘጠኝ ቀን አንገታቸውን ሲሰይፋቸው የሰማዕትነትን የድል አክሊል ተቀዳጁ።

የቅድስቲቱ ሰማዕት ቤተክርስትያኗ የከበረችበትና አብረዋት ከተጋደሉ 27 ደናግላን ጋር ሥጋቸው የፈለሰበት ዕለትም በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይከበራል። ቅድስት አርሴማ ከሃያ ሰባቱ ደናግል ጋራ ሰማዕትነት ከተቀበለች በኋላ ንጉሡ ድርጣድስ ፈጽሞ ታመመ ታወከም። በትውፊት ታላቅ ወንድሟ እንደኾነ የሚነገርለት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ሊቀ ጳጳሳትን አስቀድሞ አሥሮት ነበር። በኋላም ቅዱስ ጎርጎርዮስን ፈታውና ከደዌው ዳነ፡፡ የቅዱሳን ደናግልና የቅድስት አርሴማንም የቅዱሳን ሰማዕታቱን ዐፅመ ፍልሠታቸው ታኅሣሥ ስድስት ቀን በቅዱስ ጎርጎርዮስ ተደረገ፡፡ በስሟ ያማረ ቤተ ክርስቲያን ሠርተው አከበሩበት። ቅድስት አርሴማ በሰማዕትነት ስታርፍ ጌታችን ነፍሷን በክብር ተቀበላት ራሷን ለእርሱ በሙሽርነት አሳልፋ ሰጥታለችና ብዙ ቃል ኪዳንም ሰጣት፡፡ በዚህ ቃል ኪዳኗ የታመኑ ገዳማውያን ዘወትር አማልጂን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1