#Ethiopia | የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ በሀገሪቱ የነዳጅ ዋጋ መናር ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመመከት ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ በሰጡት ማብራሪያ፤ የኬንያን የነዳጅ ዋጋ ዝቅተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ካላቸው ጎረቤት ሀገራት ጋር ማነጻጸር ተገቢ እንዳልሆነ አስገንዝበዋል።
ፕሬዝዳንት ሩቶ ለዚህ እንደ ምክንያት ያቀረቡት ኬንያ መካከለኛ ገቢ (Middle-Income) ያላት ኢኮኖሚ መገንባቷን ነው። የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ደረጃ እና የዕድገት ምጣኔ ከጎረቤቶቿ የተሻለ በመሆኑ፣ የዋጋ ተመን ልዩነት መኖሩ ተፈጥሯዊ መሆኑን ገልጸዋል።
በኬንያ በቅርቡ የተደረገው የታክስ ማሻሻያ በነዳጅ ማደያዎች ላይ መጠነኛ የዋጋ ቅናሽ እንዲታይ ቢያደርግም፣ በህዝቡ ዘንድ ግን የክልላዊ ዋጋ ንፅፅር ክርክሮች ተቀስቅሰው ነበር። ፕሬዝዳንቱ እነዚህን ክርክሮች “ተገቢ ያልሆኑ” ሲሉ አጣጥለዋቸዋል።
እንደ ተባበሩት መንግስታት ድርጅት የ2026 ምደባ፤ እንደ ዩጋንዳ እና ታንዛኒያ ያሉ የኬንያ ጎረቤቶች አሁንም በዝቅተኛ የዕድገት ደረጃ ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ የኬንያ መንግስት ይህ የኢኮኖሚ ልዩነት በነዳጅ ምርት ግብይት ላይ የራሱ ተጽዕኖ እንዳለው እየገለጸ ይገኛል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#ቅዳሜ_ገበያ #Kenya #FuelPrice #WilliamRuto #EastAfrica #Economy #Energy #News #Ethiopia #Tanzania #Uganda
Source: GetuTemesgen








No comments yet.