ሰበር ዜናአሜሪካ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ልታነሳ ነው!የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ሰበር ዜና
አሜሪካ ኤርትራ ላይ የጣለችውን ማዕቀብ ልታነሳ ነው!
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሻሻል መንገዶችን እያሰላ መሆኑ ተሠማ። የፕሬዝዳንቱ አስተዳደር የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ ማሱድ ቡሎስ፣ የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር አሜሪካ በኤርትራ ላይ የጣለቻቸውን የተወሠኑ ማዕቀቦች የማንሳት ሂደት ለመጀመር ፍላጎት እንዳለው ለውጭ ዲፕሎማቶች መናገራቸውን ከባለሥልጣናት መስማቱን ጠቅሶ ዎል ስትሪት ጆርናል ዘግቧል።
ሌሎች ባለሥልጣናት በበኩላቸው፣ አሜሪካ ከኤርትራ ጋር ግንኙነቷን ለማሻሻልና ማዕቀቦችን ለማንሳት የያዘችው እቅድ በግምገማ ሂደት ላይ መሆኑን መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፣ ኤርትራ በፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር ሥር ከአሜሪካ ጋር ግንኙነቷን ለማሻሻል ፍላጎት እንዳላት በተደጋጋሚ ሲገልጡ ቆይተዋል።
አናዳፍታ
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: