ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ መርከቦችን ማስከፈል ጀመረች

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ዓለም አቀፉን የንግድ መስመር የሚቀይር አዲስ ክስተት! ኢራን በስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል በሚተላለፉ የንግድ መርከቦች ላይ የገንዘብ ክፍያ መሰብሰብ መጀመሯን የሀገሪቱ ፓርላማ ምክትል አፈ ጉባኤ ሃሚድሬዛ ሐጂ ባቤ ይፋ አድርገዋል።

የተሰበሰበው የመጀመሪያ ዙር ክፍያ ወደ ኢራን ማዕከላዊ ባንክ ገቢ መደረጉ ተገልጿል።

​ ክፍያው የሚወሰነው መርከቦቹ በያዙት የጭነት ዓይነትና መጠን ላይ ተመስርቶ ነው።

​ዝርዝሩ ባይገለጽም፣ ቀደም ሲል እስከ ሁለት ሚሊዮን ዶላር የሚደርስ ክፍያ ልትጠይቅ እንደምትችል ሲዘገብ ቆይቷል።

​ኢራን በወሽመጡ በኩል “ወዳጅ” የሚሏቸው ሀገራት መርከቦች ብቻ እንዲተላለፉ መፍቀዷም ተሰምቷል።

የፕሬዝዳንት ትራምፕ አስተዳደር መርከቦች ለኢራን ምንም ዓይነት ክፍያ እንዳይፈጽሙ ቀደም ብሎ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ነበር።

ይህ የኢራን እርምጃ በዓለም አቀፍ የባሕር ትራንስፖርትና በነዳጅ ዋጋ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊፈጥር እንደሚችል እየተነገረ ነው። ቢቢሲ በበኩሉ ክፍያው ስለመሰብሰቡ ከገለልተኛ ወገን ማረጋገጫ ለማግኘት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል።

ይህ የኢራን እርምጃ አሜሪካን “ዐይን ያወጣ” ፈተና ውስጥ የሚከት ነው። የሆርሙዝ ወሽመጥ የዓለም 20% ነዳጅ የሚያልፍበት በመሆኑ፣ ክፍያው ተግባራዊ ከሆነ የኑሮ ውድነቱ ዓለምን ሊያዳርስ ይችላል። ትራምፕ ለዚህ “ድፍረት” ምን ምላሽ ይሰጡ ይሆን?

​የሆርሙዝ ወሽመጥ የዓለም ፖለቲካ አዲስ የመቀጫ ጣቢያ ሆኗል!

​#getu #StraitOfHormuz #IranNews #GlobalTrade #OilPrice #TrumpVsIran #BreakingNews #MaritimeSecurity #ኢራን #ሆርሙዝ #ትራምፕ #ነዳጅ #ኢኮኖሚ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: