ኢራን በጣሊያን እንድትተካ የቀረበው አነጋጋሪ ጥያቄ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ መልዕክተኛ ኢራን በ2026ቱ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎዋ ተሰርዞ በጣሊያን እንድትተካ ለዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (FIFA) ጥያቄ አቀረቡ።

​ይህ ያልተጠበቀ ጥያቄ የቀረበው ልዩ መልዕክተኛው ፓኦሎ ዛምፖሊ ለፊፋ ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ ባስተላለፉት መልዕክት እንደሆነ ፋይናንሺያል ታይምስ ዘግቧል። ጥያቄው በዋናነት በፕሬዝዳንት ትራምፕ እና በጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ መካከል የተፈጠረውን ዲፕሎማሲያዊ ቅራኔ ለመፍታት የታለመ እንደሆነ ተገልጿል።

​በፕሬዝዳንት ትራምፕ እና በሜሎኒ መካከል አለመግባባት የተፈጠረው፣ ትራምፕ በኢራን ጦርነት ዙሪያ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛን በሰነዘሩት ትችት ሳቢያ መሆኑ ተነግሯል።

​ልዩ መልዕክተኛው ዛምፖሊ ጣሊያን አራት ጊዜ የዓለም ዋንጫን ያሸነፈች ታሪካዊ ሀገር በመሆኗ፣ በውድድሩ የመሳተፍ “ብቃት” አላት ሲሉ ተከራክረዋል። ጣሊያን ለማጣሪያው በቦስኒያ ሄርዞጎቪና ተሸንፋ ለሦስተኛ ተከታታይ ጊዜ ከዓለም ዋንጫ ውጪ መሆኗ ይታወሳል።

ኢራን በበኩሏ ለውድድሩ ዝግጁ መሆኗንና እንደምትሳተፍ በይፋ አስታውቃለች። ከዚህ ቀደም ጨዋታዎቿ ከአሜሪካ ወደ ሜክሲኮ እንዲዛወሩ ለፊፋ ጥያቄ አቅርባ እንደነበር አይዘነጋም።

​እስካሁን ፊፋም ሆነ የኋይት ሀውስ በጉዳዩ ላይ የሰጡት ይፋዊ ምላሽ የለም። ይሁን እንጂ የፊፋ ህግ አንድ ሀገር ራሷን ካገለለች ሌላ ሀገር የመተካት ሙሉ ስልጣን ለማህበሩ ይሰጣል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1