የንጹህ ውሃ ተደራሽነትን ለማፋጠን የ2.5 ቢሊዮን ዩሮ የመፍትሄ አቅጣጫ ቀረበ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja:ፌር ኤንድ ሰስቴይነብል ኢትዮጵያ (Fair & Sustainable Ethiopia) ከአኳ ፎር ኦል(Aqua for All) ጋር በመተባበር ሲያከናዉን የቆየዉን PPWASH (Potable Water, Sanitation, and Hygiene)የፋይናንስ ፕሮግራም አስመልክቶ የሥራ ሂደት የመማማርያ እንዲሁም የልምድ ልዉዉጥ መርሃ ግብር በዛሬዉ እለት በካፒታል ሆቴል ተካሂዷል፡፡

ባለፉት ዓመታት በአስር አነስተኛ የብድርና ቁጠባ ተቋማት አማካኝነት በተግባር ላይ ሲውል የቆየውን የPWASH የፋይናንስ ፕሮግራም አፈጻጸም አስመልክቶ በመድረኩ ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።

ፕሮግራሙ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የውሃና ሳኒቴሽን መሰረተ ልማቶችን በራሳቸው አቅም እንዲያሟሉ የብድር ድጋፍ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና መጫወቱ ተገልጿል።

የአኳ ፎር ኦል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ህዝቄል አይናለም እንደገለጹት፣ ድርጅታቸው በኔዘርላንድ መንግስት ድጋፍ ላለፉት አስር ዓመታት የውሃና ሳኒቴሽን ችግርን ለመቅረፍ ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል።

ፕሮግራሙ በተለይም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች የውሃና የሽንት ቤት መሰረተ ልማቶችን በራሳቸው አቅም እንዲገነቡ በብድር ድጋፍ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና መጫወቱ ተገልጿል።

በቀጣይ በአማራ ክልል 134 ሺህ የሚጠጋ ማህበረሰብን ተጠቃሚ ለማድረግ ከክልሉ መንግስት ጋር በቅርበት እየተሰራ እንደሚገኝም ተያይዞ ተገልጿል።

በኢትዮጵያ 44 በመቶ የሚሆነው ህዝብ ንጹህ ውሃ የማግኘት እድል የሌለው ሲሆን፣ 72 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በቂ የንጽህና አጠባበቅ አገልግሎት እንደማያገኙ የተገለፀ ሲሆን ይህንን ችግር ለመፍታትና የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDG 6) ለማሳካት የፋይናንስ ተቋማት ለዘርፉ ትኩረት በመስጠት መስራት እንደሚገባቸው ተመላክቷል።

በመድረኩ ላይ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ እንዲሁም ከባንክና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት የተወከሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተው የቀጣይ ትብብር ስራዎች ላይ ተወያይተዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: