ቀውሱ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ወደ ድህነት መቀመቅ ያወርዳል ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በመካከለኛው ምስራቅ እየተባባሰ የመጣው ግጭት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ30 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለከፋ ድህነት ሊዳርግ እንደሚችል የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) አስጠነቀቀ።

​ጦርነቱ በአፋጣኝ ቢቆም እንኳ፣ ቀውሱ ያስከተለው ኢኮኖሚያዊ ጠባሳ በቀላሉ የማይሻር መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

የተባበሩት መንግሥታት የልማት ፕሮግራም ኃላፊ አሌክሳንደር ዴ ክሮ ለሮይተርስ እንደገለጹት፣ ቀውሱ በተለይም በግብርናው ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አሳድሯል።

አርሶ አደሮች ሰብል በሚዘሩበት ወቅት ያጋጠመው የነዳጅ እና የማዳበሪያ አቅርቦት መቋረጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ወደ ድህነት አዘቅት ውስጥ ሊከታቸው እንደሚችል ጠቁመዋል።

​ለዚህ ችግር ዋነኛ መንስኤ ተብሎ የተጠቀሰው በሆርሙዝ ሰርጥ በኩል የሚያልፉ የጭነት መርከቦች መታገድ ነው። ይህም ለግብርና ምርታማነት ወሳኝ የሆነው የማዳበሪያ እጥረት እንዲከሰትና የምርት መጠን እንዲቀንስ አድርጓል።

​ሁኔታው በዓመቱ መጨረሻ በሚሰበሰበው የሰብል ምርት ላይ አሉታዊ ጥላውን እንደሚያሳርፍ የገለጹት ባለስልጣኑ፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለችግሩ ትኩረት እንዲሰጥ አሳስበዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#MiddleEastCrisis #GlobalEconomy #UNDP #Agriculture #PovertyAlert #BreakingNews #LeadThePlot


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: