በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ የዲጂታላይዜሽን ክፍተት መኖሩ ተጠቆመ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ኢንሹራንስ ማህበር ​ፕሬዚዳንት ያሬድ ሞላ(ዶ/ር) “ዲጂታላይዜሽን እና የደንበኞች ታማኝነት በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪ” በሚል ርዕስ ያጠኑትን የምርምር ውጤት ይፋ አድርገዋል። ጥናቱ በዘርፉ ላይ እያንዣበቡ ያሉ ስጋቶችንና መወሰድ ያለባቸውን መፍትሄዎች አመልክቷል።

​በአሁኑ ወቅት የዓለም የኢንሹራንስ አገልግሎት በትልልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችአማካኝነት ከፍተኛ ለውጥ እየታየበት ይገኛል። ጥናቱ በኢትዮጵያ ያሉ ነባር የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ከዚህ ግፊት ጋር ተያይዞ ከገበያ እንዳይወጡ ማድረግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ያተኩራል።

ዶ/ር ​ያሬድ በኢትዮጵያ የሚገኙ 18 የኢንሹራንስ ኩባንያዎችን መነሻ በማድረግ ባከናወኑት ጥናት የሚከተሉት ዋና ዋና ነጥቦች ተለይተዋል፦

-በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የኢንሹራንስ ዘርፍ ያለው የዲጂታላይዜሽን አተገባበር እጅግ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

-ደንበኞች በባንክና በቴሌኮም ዘርፎች ባላቸው ልምድ ምክንያት ለዲጂታል አገልግሎት ዝግጁ ቢሆኑም፣ የኢንሹራንስ ዘርፉ ግን ይህንን ፍላጎት ለማሟላት ወደ ኋላ ቀርቷል።

-የደንበኞችን ታማኝነት ለማረጋገጥ መጀመሪያ አገልግሎቱ ደንበኛውን ማርካት ይኖርበታል፤ ይህ ደግሞ ያለ ዲጂታላይዜሽን የማይታሰብ መሆኑ ተገልጿል።

​የኢንሹራንስ ኩባንያዎች የደንበኞችን ፍላጎት መሠረት ያደረገ፣ ለአጠቃቀም ቀላልና እምነት የሚጣልበት የዲጂታል አገልግሎት በአስቸኳይ ወደ ሥራ ሊያስገቡ እንደሚገባ በጥናቱ ተመልክቷል። ይህም ኩባንያዎቹ ያላቸውን ደንበኞች ይዘው እንዲቆዩና አዳዲስ ገበያዎችን እንዲቆጣጠሩ ይረዳቸዋል።

ዶ/ር ያሬድ ​አክለውም ኩባንያዎች ገበያቸውንና ደንበኞቻቸውን ሳያጡ በአስቸኳይ ዲጂታላይዜሽንን መተግበር አለባቸው፤ ምክንያቱም ደንበኛው ቀድሞ ዝግጁ ሆኖ እየጠበቀ ነው ብለዋል።

📸 ከበደ መክብብ

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2