#Ethiopia | ”እውቀት ለችግሮች መፍትሄ ማፍለቅ ነው!” በሚል መሪ ቃል፣ 11ኛው ከተማ አቀፍ የሳይንስ ፈጠራ ስራ አውደ ርዕይ በአዲስ አበባ በይፋ ተጀምሯል።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት አውደ ርዕዩን ሲያስጀምሩ፣ ከተማዋን የፈጠራ ማዕከል ለማድረግ የተያዘው ግብ ውጤት እያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።
የውስጥ ተሰጥኦዋቸውን በተግባር ያሳዩ ተማሪዎችና መምህራን።
ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን እውቀት ወደ ተግባራዊ መፍትሄ እንዲቀይሩ ማበረታታት።
ይህ አስደናቂ የፈጠራ ስራዎች የሚቀርቡበት አውደ ርዕይ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ይቆያል።
የከንቲባዋ ጥሪ፦ የጀመሩት የፈጠራ ስራዎች አድገው ለሀገርና ለዓለም የሚተርፉ እንዲሆኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፋቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ተማሪዎች እንዲህ ባሉ መድረኮች ሲወጡ ማየት ለሀገራችን የቴክኖሎጂ ሽግግር ትልቅ ፋይዳ አለው። ትናንት በንድፈ ሀሳብ የነበረው ዛሬ ወደ ፈጠራ ተቀይሯል። እነዚህ ተማሪዎች ነገ ዓለምን የሚቀይሩ የሳይንስ ባለሙያዎች እንደሚሆኑ አልጠራጠርም!
የነገዋ ኢትዮጵያ በዛሬው ፈጠራ ትገነባለች!
#getu #AddisAbaba #ScienceAndInnovation #InnovationExpo #STEMEthiopia #AdanechAbiebie #TechnologyEthiopia #FutureLeaders #አዲስአበባ #ሳይንስናፈጠራ #የፈጠራስራ #ትምህርት #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen



Source: GetuTemesgen









No comments yet.