በድርድር የሚጭኑ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ አሽከርካሪዎች ላይ እርምጃ መጀመሩ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ (Ride) ስምሪት ወስደው ከሲስተም ውጪ በድርድር የሚጭኑ እና በህገወጥ ታሪፍ አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥርና እርምጃ መውሰድ መጀመሩን አስታወቀ። እርምጃው በኮድ 3 የኤሌክትሮኒክስ ታክሲዎች እና በህገወጥ መንገድ በሚንቀሳቀሱ የኮድ 2 የቤት ተሽከርካሪዎች ላይ ያተኮረ ነው።

ቢሮው ባደረገው ክትትል፣ አንዳንድ አሽከርካሪዎች የድርጅት ሎጎ በመለጠፍ በተለይም ጠዋትና ማታ የሰው እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ህገወጥ ተርሚናል በመፍጠር ያለ ሲስተም በጥሪና በግምት ታሪፍ ተሳፋሪዎችን ሲጭኑ ተገኝተዋል። ይህ አሰራር ከህጋዊው የኤሌክትሮኒክስ ታክሲ ስምሪት ውጪ መሆኑ ተገልጿል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2