“ኢትዮጵያ ታምርት” የጎዳና ላይ ሩጫ

- Advertisement -
Sidebar AD

ነገ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል

#Ethiopia | ​የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር “ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 4ኛው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ነገ እሁድ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በድምቀት ይካሄዳል።

​ዓላማው
የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቃቃት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማስተዋወቅና በራስ አቅም የተመረቱ የስፖርት ትጥቆችን ለገበያ ማሳየት ነው።

​ተሳታፊዎ
ከተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ አትሌቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና በግል የሚወዳደሩ ከ15,000 በላይ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ።

​የገንዘብ ሽልማት
በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል፦

​1ኛ፦ 550,000 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር

​2ኛ፦ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር

​3ኛ፦ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር

​ይሄ ሩጫ ተራ ስፖርታዊ ውድድር አይደለም፤ የኢኮኖሚ ነጻነታችንን የምናውጅበት መድረክ ነው። ‘ኢትዮጵያ ታምርት’ በሚል መሪ ቃል የምናደርገው ይሄ ንቅናቄ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህላችንን ያሳድጋል። ነገ መስቀል አደባባይ የሚገኙ 15 ሺህ ሯጮች የሀገራቸውን ምርት እየለበሱ ለሀገራዊ ብልጽግና እንደሚሮጡ ጥርጥር የለኝም።

​ነገ መስቀል አደባባይ ለሀገር ምርትና ለጤና እንሮጣለን

​#getu #EthiopiaTamirt #IndustryEthiopia #10KRun #AddisAbabaEvents #LocalProduction #EconomicGrowth #EthiopianAthletics #ኢትዮጵያታምርት #የጎዳናላይሩጫ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1