📌
#Ethiopia | እስቲ ሁላችንም ባርኔጣችንን ከፍ አድርገን እናንሳለት፤ምክንያቱም በየጊዜው የሚሠባበሩት ሪከርዶችና ድሎቹ ለአለም የማራቶን አሠልጣኞች ንጉስ ለሆነው አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ ይሄን እንድናደርግ ያስገድዳሉና።
የቅርቡን ለጊዜው እናቆየውና አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ የሚለው ስም ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ድሎች፣ሜዳልያዎችና ሪከርዶች ጀርባ ከፍ ብሎ ሲሠማና ሲውለበለብ ይታያል
♦️2016 ሪዮ ኦሎምፒክ
🥉በ10ሺ ሜትር
በአትሌት ታምራት ቶላ የነሐስ ሜዳልያ
♦️በ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ በማራቶን
🥇በአትሌት ታምራት ቶላ(ወርቅ)
🥈በአትሌት ትዕግስት አሠፋ(ብር)
♦️በ2009 የአለም ሻምፒዮና በርሊን በማራቶን
🥉አትሌት አሠለፈች መርጊያ(ነሐስ)
♦️በ2017 የአለም ሻምፒዮና በርሊን በማራቶን
🥈አትሌት ታምራት ቶላ (ብር)
♦️በ2022 የአለም ሻምፒዮና አሜሪካ ኦሪገን በማራቶን
🥇አትሌት ታምራት ቶላ (ወርቅ)
♦️በ2023 የአለም ሻምፒዮና ሀንጋሪ ቡዳፔስት በማራቶን
🥇አትሌት አማኒ በሪሶ (ወርቅ)
♦️WR አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በ21ኪ.ሜ አዲስ ሪከርድ
♦️አትሌት ትዕግስት አሠፋ ሶስት ጊዜ የአለም ሪከርድ ባለቤት
♦️በቅርቡ ደግሞ አትሌት ፎቴን ተስፋይ ሁለተኛው የማራቶን ምርጥ ሠዓት ሪከርድ ባለቤት
ከእነዚሁ ሁሉ ስኬቶችና ሪከርዶች ጀርባ በውጤት ያሸበረቀ በወርቅ ቀለም ስሙን በደማቁ ያፃፈ የሀገር ኩራት የሆነ ታላቅ ሠው አለ እሱም አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ።
ዛሬም በለንደን ሠማይ ስር በማራቶን ታሪክ ሲሠራ የእሱ የስልጠና በረከት ያረፈባቸው አትሌት ትዕግስት አሠፋ አንደኛ ከመውጣት በተከታታይ ዓመት የለንደንን ማራቶን ከማሸነፍ በዘለለ በሴቶች ብቻ(Only Womens)ተይዞ የነበረውን የራሷን ሪከርድ አሻሽላለች።
ሌላኛው የአሠልጣኝ ገመዶ የስልጠና ውጤት የሆነው አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በመጀመሪያው የማራቶን ተሳትፎው ሁለተኛ ከመውጣት ባለፈ የሠው ልጅ በዚህ ዘመን ማራቶንን ከ2:00:00 በታች እንደሚገባ በተግባር ካሳየው ዮሚፍ ቀጄልቻ ጀርባም ይሄ የአለማችን የማራቶን አሠልጣኞች ንጉስ ገመዶ ደደፎ አለ።
የአሸናፊነትና የሪከርዶች ባለቤት ከሆኑት አትሌቶች ጀርባ ወይም የውጤታማነት ምስጢራቸው የሆነው የአሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ ስም ዛሬም እንደ ትላንቱ እንደ ባንዲራ ከፍ ብሎ ሲውለበለብ ይታያል።
👉የስኬታማና የሪከርድ ሠባሪ አቴሌቶችን ስም አንስተን ገመዶ ደደፎ የሚለውን ስም አለማንሳት የሀገር ባለውለታውን ውለታ ከመብላቴም ያስቆጥራል።
እንኳን ደስ አለህ!! አሠልጣኝ ገመዶ ደደፎ
✍️✍️በጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ(ሀትሪክ ስፖርት ኦፊሺያል)


Source: GetuTemesgen









No comments yet.