ደም በመለገስ የእናቶችን ሕይወት እንታደግ! — ከቡና ደጋፊዎችና ከኮሌጃችን የቀረበ ጥሪ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ታላቅ የሰብዓዊነት መርሐ ግብር! ኮሌጃችን ከ”ኳስ ሜዳ እና አካባቢው የቡና ደጋፊዎች መረዳጃ ዕድር” ጋር በመተባበር ልዩ የደም ልገሣ መርሐ ግብር አዘጋጅቷል።

ይህ ልገሣ በተለይ በወሊድ ወቅት ደም ለሚያስፈልጋቸው እናቶቻችን ሕይወት መትረፍ ታስቦ የተዘጋጀ ነው። አንድ ጠብታ ደም የአንዲት እናትን ሕይወት፣ የአንድን ቤተሰብ ተስፋ ሊያድን ይችላል።

​ መቼና የት?

ነገ ሚያዚያ 18/2018 ዓ.ም (እሁድ)

ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ

በኮሌጁ ቅጥር ግቢ — ዋናው ሕንጻ መግቢያ

የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊነት በስታዲየም ጩኸት ብቻ አይገደብም፤ እንዲህ ባሉ ወሳኝ የሕይወት አድን ተግባራት ላይም ግንባር ቀደም መሆንን ይጠይቃል።

ነገ ጠዋት ሁላችንም በኮሌጃችን ቅጥር ግቢ በመገኘት ደም በመለገስ ለወገኖቻችን አለኝታነታችንን የምናሳይበት ዕለት ነው። እናቶችን ማዳን ትውልድን ማዳን ነው!

​ደምዎን ይለግሱ፣ ሕይወት ይታደጉ!

​#getu #BloodDonation #EthiopiaBunna #SaveMothers #CommunityService #AddisAbaba #Humanitarian #LifeSaving #ደምልገሣ #እናቶችንእናድን #ኢትዮጵያቡና #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1