ሁለት መኪናዎችን በእጣ ያሸነፈው ዕድለኛ ኢንስፔክተር

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​ኢንስፔክተር ጂልቻ ከፉሪ በአንድ ሳምንት የጊዜ ልዩነት ውስጥ በተለያዩ ከተሞች በሚወጡ የመኪና እቁብ እጣዎች የሁለት ተሽከርካሪዎች ባለቤት በመሆን ዕድለኛ ሆነዋል።

​ኢንስፔክተሩ መጀመሪያ በሆሳዕና ከተማ በሚዘጋጀው “ቪክቶር ሰለሜ” የመኪና እቁብ የFord F150 (ፎርድ) መኪና እጣ የደረሳቸው ሲሆን፣ ይህ ደስታ ሳይረሳ በጥቂት ቀናት ልዩነት ደግሞ በአዳማ ከተማ በሚዘጋጀው “ዳኒ አዳማ” የመኪና እቁብ የHyundai Creta (ዩንዳይ) መኪና ዕድለኛ መሆናቸው ታውቋል።

​ግለሰቡ በአዳማው የመኪና እቁብ ከዚህ ቀደም የ50 ሺህ ብር እጣ አሸናፊ እንደነበሩ የተነገረ ሲሆን፣ አሁን ግን በጥቂት ቀናት ውስጥ የሁለት ዘመናዊ መኪናዎች ባለቤት መሆን ችለዋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1