ህፃን ልጅ ላይ የግብረ ስጋ ድፍረት የፈፀመው ግለሰብ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​በአምስት ዓመት ህፃን ላይ አስቃቂ የግብረ ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የሠገን ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔ አሳለፈ።

​ተከሳሹ አቶ ሲዳሞ ገልገሎ የቀረበበትን የወንጀል ክስ “አልፈፀምኩም” ብሎ ቢክድም፣ የሠገን ዙሪያ ወረዳ ፍትህ ጽሕፈት ቤት ዓቃቤ ህግ ተከሳሹ ወንጀሉን ስለመፈፀሙ የሚያስረዱ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል። ተከሳሹ መከላከያ ማስረጃ የለኝም በማለቱ ፍርድ ቤቱ ጥፋተኛነቱን አረጋግጧል።

​በዚሁ መሠረት ፍርድ ቤቱ ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት፣ ግለሰቡ በፈፀመው የከፋ ወንጀል ተጸጽቶ እንዲታረም እና ሌሎች መሰል እኩይ ተግባር እንዳይፈጽሙ ትምህርት እንዲሆን በ19 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

​የፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ተመስገን ተስፋዬ በሰጡት መግለጫ፣ ተቋሙ በሴቶችና በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ለመከላከል ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ህብረተሰቡ ህፃናትን ከእንዲህ ዓይነት ጥቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1