በ3.5 ሚሊዮን ብር የተሰራው የፀጋዘአብ ገ/ስላሴ አዲስ አልበም የፊታችን ሐሙስ ለገበያ ይቀርባል

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ታዋቂው የትግርኛ ሙዚቃ ድምጻዊ ፀጋዘአብ ገ/ስላሴ “ንጉስ ዳግማይ ንጉስ” የተሰኘውን 4ኛ የሙዚቃ አልበሙን የፊታችን ሐሙስ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚለቀቅ በዛሬው እለት በካፒታል ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ።

አልበሙ በድምሩ ከ3.5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ሲሆን፣ ስራውን አጠናቆ ለአድማጭ ለማቅረብ ሁለት ዓመታትን መፍጀቱ ተገልጿል። አልበሙ 12 የሙዚቃ ስራዎችን የያዘ ሲሆን፣ በይዘቱም በፍቅር፣ በማህበራዊ ህይወት እና በባህል ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው።

ከአንዱ የህዝብ ዜማ ውጪ የሁሉም 12ቱ ሙዚቃዎች ግጥምና ዜማ የተደረሰው በራሱ በድምጻዊ ፀጋዘአብ ገ/ስላሴ ነው። አልበሙ በድምጻዊው የዩቲዩብ ቻናል (ናዶና – Nadona) እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የዲጂታል የሙዚቃ መተግበሪያዎች ላይ ይለቀቃል።

ፀጋዘአብ ገ/ስላሴ ቀደም ሲል “እምበይተይ” በተሰኘው ተወዳጅ የሙዚቃ ስራው በአድማጮች ዘንድ ሰፊ እውቅናን ያተረፈ ድምጻዊ ነው።

የዝግጅቱን ጋዜጣዊ መግለጫ ኤርሚ ኤቨንት ከዳይናሚክ ኢንተርቴይመንት ጋር በመተባበር አዘጋጅተውታል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: