ነገ በመስቀል አደባባይ ይካሄዳል
#Ethiopia | የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር “ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው 4ኛው የ10 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ፣ ነገ እሁድ ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በመስቀል አደባባይ በድምቀት ይካሄዳል።
ዓላማው
የሀገር ውስጥ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ማነቃቃት፣ የሀገር ውስጥ ምርትን ማስተዋወቅና በራስ አቅም የተመረቱ የስፖርት ትጥቆችን ለገበያ ማሳየት ነው።
ከተለያዩ ክለቦች የተውጣጡ አትሌቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶችና በግል የሚወዳደሩ ከ17ሺ በላይ ተሳታፊዎች ይጠበቃሉ።
በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ለሚሆኑ አትሌቶች ከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት ተዘጋጅቷል፦
1ኛ፦ 550,000 (አምስት መቶ ሃምሳ ሺህ) ብር
2ኛ፦ 300,000 (ሶስት መቶ ሺህ) ብር
3ኛ፦ 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ) ብር
‘ኢትዮጵያ ታምርት’ በሚል መሪ ቃል የምናደርገው ይሄ ንቅናቄ፣ የሀገር ውስጥ ምርትን የመጠቀም ባህላችንን ያሳድጋል። ነገ መስቀል አደባባይ የሚገኙ 17ሺ ሯጮች የሀገራቸውን ምርት እየለበሱ ለሀገራዊ ብልጽግና እንደሚሮጡ ጥርጥር የለውም።
ነገ መስቀል አደባባይ ለሀገር ምርትና ለጤና እንሮጣለን
#getu #EthiopiaTamirt #IndustryEthiopia #10KRun #AddisAbabaEvents #LocalProduction #EconomicGrowth #EthiopianAthletics #ኢትዮጵያታምርት #የጎዳናላይሩጫ #አዲስአበባ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen



Source: GetuTemesgen









No comments yet.