ማንችስተር ዩናይትድ ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመመለስ የሚያስችለውን እጅግ ወሳኝ ውጤት አገኘ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ34ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድትራፎርድ ብሬንትፎርድን አስተናግዶ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

በጨዋታው ካሲሚሮ እና ቤንጃሚን ሼስኮ የዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ሲያስቆጥሩ ለብሬንትፎርድ ብቸኛዋን ግብ ማቲያስ የንሰን አስቆጥሯል።

ምንም እንኳን ብሬንትፎርድ የኳስ ቁጥጥር የበላይነት ቢኖረውም የተገኙትን አጋጣሚዎች በአግባቡ የተጠቀመው ማንችስተር ዩናይትድ ነጥቡን ይዞ መውጣት ችሏል።

ይህ ውጤት ዩናይትድ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ61 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ እንዲቀመጥና ለቀጣዩ ዓመት የሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ እጅግ እንዲቃረብ አድርጎታል።

በሌላ በኩል ሽንፈት የገጠመው ብሬንትፎርድ በ48 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ባለፉት ስድስት ጨዋታዎች ድል መራቆቱን ቀጥሏል።

በዚህ ጨዋታ ላይ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለቤንጃሚን ሼስኮ ግብ መሆን ምክንያት የሆነችውን ኳስ በማቀበል በውድድር ዓመቱ ለጎል የሚሆኑ ኳሶችን የማመቻቸት ብዛቱን ወደ 19 አሳድጓል።

የ34ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በዚህ ውጤት የተጠናቀቁ ሲሆን የ35ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የሚቀጥል ይሆናል።

#manchesterunited #brentford #premierleague #football #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: