#FastMereja I የቀድሞው የአርሰናል እና የአሁኑ የቪያሪያል ተጫዋች ኒኮላስ ፔፔ፣ ከታዋቂዋ የወሲብ ፊልም ተዋናይ ቲያና ትራምፕ ጋር የጋብቻ ጥያቄ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑን የቱርክ መገናኛ ብዙሃን ዘገቡ። ለአንድ ዓመት ተኩል የዘለቀው ይህ የፍቅር ግንኙነት፣ አሁን ወደ ትዳር የመሸጋገር ከፍተኛ ዕድል እንዳለው ታውቋል።
እንደ ቱርክ ‘Kuzey Ekspres’ ዘገባ ከሆነ፣ በቱርክ ትራብዞንስፖር ሲጫወት የነበረው ፔፔ ከ30 ዓመቷ ኬና ኒሼል ጆንስ (በመድረክ ስሟ ቲያና ትራምፕ) ጋር ያለው ግንኙነት እጅግ ጠንካራ መሆኑን ለቤተሰቦቹ ገልጿል። ፔፔ ስለ እሷ ሲናገር “የህይወቴ ፍቅር ናት” ማለቱ የተዘገበ ሲሆን፣ ትዳሩ ከተፈጸመ በኋላም ተዋናይቷ ከስራዋ እንድትገለልና “የቤት እመቤት” እንድትሆን ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል።
ቲያና ትራምፕ በወሲብ ፊልም ስራ የ11 ዓመታት ልምድ ያላትና በኢንስታግራም ብቻ ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ተከታዮች ያሏት ሲሆን፣ የፔፔ ውሳኔ በቱርክ እና በአውሮፓ እግር ኳስ አፍቃሪዎች ዘንድ መነጋገሪያ ሆኗል። ይህ ጋብቻ እውን ከሆነ ለፔፔ ሁለተኛው ይሆናል። ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ከፈረንሳይኛ ተናጋሪዋ ኢንፍሉዌንሰር ፋኒ ቢ ጋር ትዳር መስርቶ የነበረ ሲሆን፣ በ2024 ግንኙነታቸው መቋረጡ ይታወሳል።
Source: FastMereja









No comments yet.