ከሀገር ውጭ የአካል ንቅለ ተከላ ለሚያደርጉ ታካሚዎች የአንድ ሚሊዮን ብር የባንክ ተቀማጭ ግዴታ ተጣለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ለአካል ንቅለ ተከላ ህክምና ወደ ውጭ ሀገር መጓዝ ለሚፈልጉ ዜጎች አንድ ሚሊዮን ብር በዝግ የባንክ ሂሳብ እንዲያስቀምጡ የሚያዝ አዲስ መመሪያ ስራ ላይ ዋለ።

ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆነው የሚፈለገው የህክምና አገልግሎት በሀገር ውስጥ የማይሰጥ መሆኑ በልዩ የህክምና ቦርድ ሲረጋገጥ ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

ከገንዘብ መጠኑ በተጨማሪ ታካሚዎች በህግ ፊት የጸደቀ የለጋሽ ስምምነት ሰነድ ማቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ይህም ህገወጥ የሰዎች እና የአካል ክፍሎች ዝውውርን ለመከላከል የታለመ ነው።

ይሁን እንጂ በሀገር ውስጥ ያለው የህክምና መጠባበቂያ ጊዜ ለታካሚው ህይወት አስጊ መሆኑ ከተረጋገጠ ልዩ ሁኔታዎች ሊታዩ እንደሚችሉ በመመሪያው ተመልክቷል።

በሌላ በኩል የውጭ ሀገር የህክምና ተቋማትን ወክለው መስራት የሚችሉት ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የጤና ባለሙያዎች ብቻ መሆናቸውን አዲሱ መመሪያ ይደነግጋል።

እነዚህ ወኪሎች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የተቋማቱን የዕውቅና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ይህ አሰራር በዘርፉ የሚታየውን ያልተገደበ እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እና የታካሚዎችን ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠበቅ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑ ተጠቁሟል።

#ጤና #የጤናጥበቃ #ህክምና #ንቅለተከላ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1