ከተራሮች አናት ሁሉ ከፍ ያለች ስትሆን ራሷን ዝቅ አድርጋ

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

በመጽሐፍ ቅዱስ የእናታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ያህል ትንቢት የተነገረላት ስለእርሷ የተጻፈላት ሴት የለችም። በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ብዙ ምሳሌዎች ተጠቅሰዋል፤ የኖኅ መርከብ፣ ሰላማዊት ርግብ፣ የአብርሃም ድንኳን፣ ሙሴ በሲና ያያት ሐመልማል፣ ጽላተ ሙሴ፣ የኢያሱ የምስክርነት ሐውልት፣ የኤልያስ የወርቅ መሶብ፣ የአሮን በትረ፣ የጌዴዎን ፀምር፣ የኖኅ የቃል ኪዳኑ ቀስተ ደመና፣ ያዕቆብ በፍኖተ ሎዛ ያያት መሰላል፣ የነቢዩ ኤልሳዕ ማሰሮና ሌሎች ምሳሌዎች በሰፊው የተነገሩላት የተጻፉላት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት። ቤተ ክርስቲያን እርስዋን ለመጥራት የምትጠቀምባቸው ቅጽል ስሞቿና ውዳሴዎቿ ምንኛ ድንቅ ቢሆኑ በመጽሐፍ ቅዱስ መንፈስ ገላጭነት በቅዱሳን የተነገሩ ምስጋናዎቿስ እጅግ ቢለዩ የክብሯን ያህል የሚገልጿት አይደሉም፡፡

እርሷ የሰው ሁሉ ረዳትና ርኅሩኅ እናት ናት፤ የብርሃን፣ የምሕረት፣ የድኅነትና የአማናዊው ወይን እናት ናት። ከንጉሡ በስተቀኝ የምትቆመው ንግሥት እርስዋ ናት፤ በመስቀል ስር የተቀበልናት የሁላችንም እናት እርሷ ናት፤ እርሷ ዘለዓለማዊ ድንግል ናት፤ እርሷ የእግዚአብሔር ጸጋ የሞላባት ንጽሕት ቅድስት ድንግል ናት፡፡ ከፍጥረት ሁሉ ተለይታ ወላዲተ አምላክ ለመሆን የተመረጠችበት አንዱ ምክንያት እመቤታችን እጅግ ትሑት፣ ፍጽምትና ንጽሕት ስለሆነች ነው። በሉቃስ 1÷48 እንደተጻፈው የአምላክ እናት እንደምትሆን ተነግሯት እንኳን ክብር ይግባትና ከመኩራትና ሌሎችን ከመናቅ ይልቅ ዘመዷ ኤልሳቤጥን ልትጠይቃት ወደ ተራራማው አገር ወደ ይሁዳ ወጣች፡፡ ከኤልሳቤጥ ፍጹም ምስጋናና በማሕጸን ያለው ዮሐንስ የሰላምታ ድምጿን ሰምቶ መዝለሉንከሰማች በኋላም “የባሪያይቱን መዋረድ ተመልክቷልና” በማለት በትሕትና ምስጋናዋን አቀረበች እንጂ የትዕቢት ቃል ከአፏ አልወጣም፡፡

ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ “እርሷ በእግዚአብሔር ዓይን በታየ የቅድስና ውበት የተሞላች ነበረችና በእርሷ ንጹሕ ማሕፀን ሊያድር ወደደ፤ እንደ ድንግል ማርያም ራሱን ዝቅ ያደረገ ትሑት ማንም የለም” ይላል። ቅዱስ ኤፍሬም በውዳሴ ማርያም “በትሕትና የተናገርሽ ተራራ ሆይ…” ብሎ ያመሰገናት ይህች ድንግል “እንዲህ ያለ የምስጋና እጅ መንሻ እንደምን ይደረግልኛል” የሚል ምላሽ ለቅዱስ ገብርኤል ሰጠችው፡፡ እመቤታችን ቅድስት ማርያም ዓለምን ፈጥሮ የሚገዛው አምላክ ልጇ ነውና ማርልኝ ስትለው ምልጃዋ ፍጹም ነው፡፡ በእግዚአብሔር መመረጧ፣ ከሴቶች ሁሉ መለየቷ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ መሆኗ ይህን ክብር አጎናጽፏታልና፡፡ ገዳማውያንም ይህን ልዩ እናትነቷንና ቅድስናዋን አምነው ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሯታል፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ፣ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: