በኢትዮጵያ የወረርሽኝ ስጋትን በ24 ሰዓት ውስጥ ሪፖርት የሚያደርግ ሥርዓት መዘርጋቱ ተበሰረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I በኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት በመጀመሪያ ደረጃ ጤና ጥበቃ ተቋማት ላይ ሲተገበር የቆየውና ወረርሽኞችን ቀድሞ የመለየትና የመከላከል አቅምን ለማሳደግ ያለመው “Epidemic-Ready Primary Health Care” (ERPHC) የተሰኘው ተነሳሽነት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡ ተገለጠ።

በጤና ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ የሕዝብ ጤና ኢንስቲትዩት እና “Resolve to Save Lives” ከተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት ጋር በመተባበር ሲተገበር የቆየው ይህ ፕሮጀክት፤ በአዲስ አበባ፣ በሲዳማና በደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች በሚገኙ 197 የጤና ተቋማት ላይ ውጤታማ ስራዎችን ማከናወኑ ነው የተነገረው።

ወረርሽኞችን በ7 ቀናት ውስጥ የመለየት፣ በ1 ቀን ውስጥ የማሳወቅ እና በ7 ቀናት ውስጥ ምላሽ የመስጠት ግብ (7-1-7) ውጤታማ በሆነ መንገድ ተተግብሯል። ለዚህም ማሳያ በሶስቱ ክልሎች የተከሰቱ 62 የህክምና ጉዳዮች 100% በሚባል ደረጃ በ7 ቀናት ውስጥ ተለይተው በ24 ሰዓታት ውስጥ ሪፖርት ተደርገዋል ተብሏል።

ከ14,850 በላይ የጤና ባለሙያዎች በስራ ላይ ስልጠና (Mentorship) እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን፣ ይህም የተቋማቱን ዝግጁነት ከ47% ወደ 80% አሳድጎታል።

በተካሄደው የ”Mystery Patient” ወይም የድብቅ ታካሚ ፍተሻ፣ በፕሮጀክቱ የታቀፉ የጤና ተቋማት ካልታቀፉት እጅግ የተሻለ ዝግጁነት እንዳላቸው በተጨባጭ ተረጋግጧል። በዝግጅቱ ላይ የተገኙ የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች ይህ ተሞክሮ ዘላቂነት እንዲኖረውና ወደ ቀሪ የሀገሪቱ ክፍሎች እንዲሰፋ ጥሪ አቅርበዋል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1