#Ethiopia | የማንችስተር ዩናይትድ የካሪንግተን ተረኛ ኮከብ ኮቢ ማይኖ በክለቡ ያለውን ቆይታ የሚያራዝም አዲስ ውል መፈረሙ ተረጋገጠ።
ወጣቱ እንግሊዛዊ አማካይ በኦልድትራፎርድ እስከ 2031 ድረስ ለመቆየት የሚያስችለውን ስምምነት በዛሬው እለት ያከናወነ ሲሆን፣ ክለቡ ለተጫዋቹ ብቃት እውቅና በመስጠት ከፍተኛ የደሞዝ ጭማሪ ማድረጉ ተገልጿል።
በዚህም መሰረት የ21 ዓመቱ ማይኖ አሁን ላይ በክለቡ የመጀመሪያ ቡድን ውስጥ ካሉ ከፍተኛ ተከፋይ ተጫዋቾች ጋር የሚመጣጠን የደሞዝ እርከን ላይ እንዲቀመጥ ተደርጓል።
ባለፈው የጥር የዝውውር መስኮት በውሰት ለመውጣት ተቃርቦ የነበረው ማይኖ፣ በአሰልጣኝ ማይክል ካሪክ ስር አስደናቂ የሚባል መነሳሳትን አሳይቷል። ካሪክ ቡድኑን በኃላፊነት ከመሩባቸው ያለፉት 13 የሊግ ጨዋታዎች መካከል በ12ቱ ላይ ማይኖ በቋሚነት ተሰልፎ መጫወት የቻለ ሲሆን፣ አንድ ጨዋታ ብቻ በጉዳት ምክንያት አምልጦታል።
ይህ አዲስ ስምምነት ማንችስተር ዩናይትድ የወደፊት የቡድን ግንባታውን በማይኖ ዙሪያ ለማድረግ ማቀዱን የሚያሳይ ትልቅ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#KobbieMainoo #ManchesterUnited #MUFC #TransferNews #MichaelCarrick #EPL #Carrington #ManUtd_Update
Source: GetuTemesgen









No comments yet.