ለተፈቀደላቸው ሁሉ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ይገልጣል

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33፥7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል” በማለት እንደተናገረ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩት ሰዎች በጨነቃቸው ጊዜ በመካከላቸው እየተገኘ ያጽናናቸዋል። ምሥጢር ይገልጥላቸዋል፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቃቸዋል። ዑራኤል ማለት “ብርሃነ እግዚአብሔር” ማለት ነው። ዑራኤል በብርሃናት ላይ ሁሉ የተሾመ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6፥2 “ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ የተሾመ ነው” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ከሊቃነ መላእክት አንዱ መሆኑንና ፍርሃት ረዓድ ላለባቸው ረዳታቸው እንደሆነ የመላእክትን ነገር የተናገረ ሄኖክ ነግሮናል፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ገላጭ ነው።

ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ግልጽ ነው። የተወደደ ሥራ ለሚሠሩና እንዲያውቁ ፡፡ በመጽሐፈ ዕዝራ ሱትኤል 13፥38 እንደተጻፈው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ዕዝራ ሱቱዔልን “አፍህን ክፈት፤ እኔም የማጠጣህን ጠጣ” ብሎ ሐምሌ 22 አእምሮና ማስተዋልን ገልጦለታል። ለሄኖክም ምሥጢረ ሰማይንና ዕውቀትን የገለጠለት እርሱ ነው፡፡ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ልቡናውን ያበራለት ይህ መልአክ እንደሆነ ገዳሙ ባሳተመው ገድሉ ላይ ተጽፏል። በዚህ አገልግሎቱም ሊቃውንቱ “ከሣቴ ምሥጢር” ወይም “ምስጢርን የሚገልጽ” ይሉታል። አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል የሚናገሩ ሁሉ ክብርና ጥበቃን ከመላእክት ይቀበላሉ፡፡

ዕዝራ ለረጅም ወራት እግዚአብሔርን ደጅ ጸንቶ ነበር። የነገሩትን የማይረሳ እግዚአብሔር መልአኩን ላከለት፤ የሰማዩን ምሥጢርም ዐወቀ። ይህ መልአክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ በመካከላቸው ሁኖ መንገድ ይመራቸው እንደነበር በድርሳነ ዑራኤል ተገልጿል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ደሙን በፈቃዱ ሲያፈስም በጽዋዕ የተቀበለው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል መሆኑን በዕለተ ዓርብ በሚነበበው ግብረ ሕማማት ተጽፏል። በሊቀ መላእክትነት የተሾመበት በዓል ጥር 22፣ ከጌታችን የፈሰሰውን ደም በጽዋዕ የተቀበለበት መጋቢት 27 ቀን ይከበራል። ገዳማውያን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፣ እርሱም ይራዳቸዋል፤ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1