ባይናንስ በኢትዮጵያ ብር የሚደረግ የንግድ ልውውጥን ለጊዜው ሊያግድ መሆኑን አስታወቀ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#Ethiopia | በዓለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ የሆነው የክሪፕቶ ምንዛሬ መገበያያ መድረክ ባይናንስ ፣ ከግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በኢትዮጵያ ብር የሚደረጉ ማንኛቸውም የንግድ ልውውጦች ለጊዜው እንደሚታገዱ በይፋ አስታወቀ።

​ባይናንስ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የንግድ ልውውጡ ቢታገድም የተጠቃሚዎች ገንዘብ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑንና ደንበኞች በማንኛውም ጊዜ ወደ አካውንታቸው በመግባት የገንዘብ እንቅስቃሴያቸውን መከታተል እንደሚችሉ አረጋግጧል።

ይህ ውሳኔ የተላለፈው የኢትዮጵያን ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ውሳኔዎች ለመደገፍና ከሚመለከታቸው የቁጥጥር ተቋማት ጋር በቅርበት ለመስራት ካለው ፍላጎት በመነሳት እንደሆነም ተቋሙ ገልጿል።

​የኢትዮጵያ ብር የንግድ ልውውጥ አገልግሎትን በቅርቡ ዳግም ለመጀመር ተስፋ ማድረጉን የጠቀሰው ባይናንስ አፍሪካ፣ ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ አዳዲስ መረጃዎችንና ማሻሻያዎችን ለተጠቃሚዎቹ በየጊዜው እንደሚያጋራ አስታውቋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#Binance #Ethiopia #ETB #CryptoMarket #BinanceAfrica #FinanceNews #CryptoCurrency #EthiopianBirr


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: