አሜሪካ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን ሁለት የኢራን የነዳጅ መርከቦች ልትወርስ ነው​የአሜሪካ መንግስት ባለፉት ሳምንታት በባህር ኃ…

- Advertisement -
Sidebar AD
አሜሪካ በቁጥጥር ስር ያዋለቻቸውን ሁለት የኢራን የነዳጅ መርከቦች ልትወርስ ነው
​የአሜሪካ መንግስት ባለፉት ሳምንታት በባህር ኃይሏ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሁለት የኢራን የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን በቋሚነት ለመውረስ የህግ ሂደት መጀመሩን ብሉምበርግ የዋይት ሃውስ ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጠቅሶ ዘግቧል።

መርከቦቹ M/T Majestic X Phonix በእና M/T Tifani የተሰኙት ግዙፍ የነዳጅ ጫኝ መርከቦች ናቸው።መርከቦቹ የተያዙት ባለፈው ሳምንት በህንድ ውቅያኖስ (በሲሪላንካ አቅራቢያ) ሲሆን፣ ወደ 3.8 ሚሊዮን በርሜል የሚጠጋ የኢራን ድፍድፍ ነዳጅ ጭነው እንደነበር ተገልጿል።
​ የአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር  መርከቦቹን እና ነዳጁን ለዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ገቢ ለማድረግ ክስ መስርቷል። ኢራን ድርጊቱን “የባህር ላይ ዘረፋ”  ስትል የጠራችው ሲሆን፣ የአሜሪካ እገዳ የማይቆም ከሆነ “ከባድ ወታደራዊ እርምጃ” እንደምትወስድ አስጠንቅቃለች።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: