የአሜሪካ ድርጊት «የማይሳካ» ነው – ፕረዚደንት ሞሱድ ፐዛሽኪያን የኢራን ፕረዚደንት አሜሪካ እያካሄደች ያለውን የሆርሙዝ ሰርጥ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የአሜሪካ ድርጊት «የማይሳካ» ነው – ፕረዚደንት ሞሱድ ፐዛሽኪያን
የኢራን ፕረዚደንት አሜሪካ እያካሄደች ያለውን የሆርሙዝ ሰርጥ ክልከላ በፐርሺያ ባሕረሰላጤ አለመረጋጋትን የሚያሰፍን ነው ሲሉ ወቀሱ።
ፕረዚደንት ሞሱድ ፐዛሽኪያን ዛሬ ባሰራጩት መልዕክት የአሜሪካን ድርጊት «የማይሳካ» ብለውታል።
የአሜሪካው ፕረዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ደሴቶች የሚወጡም ሆነ የሚገቡ መርከቦች እንቅስቃሴ እንዲታጎል የሰጡትን መመሪያን ተከትሎ በሁለቱም አገራት ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ድርድር ለመክሸፉ እንደአንድ ምክንያት ሊሆን መቻሉን መረጃዎች ያመላክታሉ።
ኢራን ክልከላው እንዲነሳ፣ ጦርነቱ ቆሞ የደሕንነት ዋስትና እንዲሰጣት እንዲሁም የኒኩሌር ማበልጸግ ጉዳይ ወደፊት የሚታይ አጀንዳ እንዲሆን የሚሉ የመደራደሪያ ነጥቦችን በፓኪስታን በኩል ወደ አሜሪካ ልካለች።
ዩናይትድ ስቴትስ መደራደሪያ ነጥቦቹ እያጤንኳቸው ነው ብትልም ባሕር ሐይሏ ግን ከኢራን ወደቦች የሚወጡና የሚገቡትን መከልከሉን እንደቀጠለ ነው።
ይህን ተከትሎ ነው ፕረዚደንቱ በመግለጫቸው ክልከላው ለቀጠናው አደገኛ አለመረጋጋትን ያስከትላል ሲሉ ያስጠነቀቁት።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2