#FastMereja I ለሦስት ዓመታት በኢቢኤስ (EBS) ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የነበረው ታዋቂው “በስንቱ” ድራማ፣ ወደ ቻናል ዋን (Channel 1) ተዛውሮ የመጀመሪያውን ክፍል ካሳየ በኋላ በቀጣይ እንዳይተላለፍ በፍርድ ቤት እግድ ተጣለበት። እግዱ የተላለፈው በኢቢኤስ እና በአብሪኮ መልቲ ሚዲያ መካከል በተፈጠረ የባለቤትነት መብት ክርክር ምክንያት እንደሆነ ታውቋል።
የሁለቱ ተቋማት አለመግባባት ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱን ተከትሎ፣ ከሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በቻናል ዋን መታየት የጀመረው ድራማው ከአንድ ክፍል በላይ ሊቀጥል አልቻለም። ከእግዱ ጋር ተያይዞ በቀጣይ ሊሰሩ የነበሩ የቀረጻ ስራዎችም ለጊዜው እንዲቆሙ ለአርቲስቶቹ ተነግሯቸዋል።
በሌላ በኩል አብሪኮ መልቲ ሚዲያ በኢቢኤስ ላይ የፍትሐ ብሔር ክስ የመሰረተ ሲሆን፣ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ ችሎት የሁለቱን ወገኖች ክርክር ለመስማት ለግንቦት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቷል ሲል ኢትዮጲካሊንክ ነው የዘገበው።
Source: FastMereja









No comments yet.