ለአምስት ተከታታይ ቀናት ከሥራ የቀረ ሠራተኛ ያለ ማስጠንቀቂያ ከሥራ እንደሚሰናበት በሰበር ችሎት የተሰጠው የሕግ ትርጓሜ፣ በአዋጁ ላይ ያለውን ግልጽ አሠራር መሠረት ያደረገ መሆኑ ተገለጸ
የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) እንዳስታወቀው፣ በአሠሪና ሠራተኛ አዋጅ እንዲሁም በኅብረት ስምምነት ከተቀመጡት የፈቃድ ዓይነቶች ውጭ ለ5 ተከታታይ ቀናት ከሥራ የቀረ ሠራተኛ ከሥራ እንደሚሰናበት በግልጽ ተቀምጧል።
የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ የሰበር ችሎት በጉዳዩ ላይ የሰጠው ትርጓሜ አዲስ ሕግ ሳይሆን በአዋጁ ላይ ያለውን አሠራር የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም፣ ከተፈቀዱ ሕጋዊ ፈቃዶች ውጭ አንድ ሠራተኛ በራሱ ምክንያት ለ5 ተከታታይ ቀናት ከሥራ ከቀረ አሠሪው ሕጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚችል አዋጁ በግልጽ ያስቀምጣል ብለዋል። ሰበር ችሎትም ሕጉን ሲተረጉም አዲስ ነገር ሳይሆን በአዋጅና በኅብረት ስምምነት ያለውን አሠራር በመከተል መሆኑን ጠቁመዋል።
ይሁን እንጂ እርምጃው በሚወሰድበት ወቅት በሕግ የተፈቀዱ እንደ ሐዘን፣ የወሊድ እና የሕክምና ፈቃድ የመሳሰሉትን አካቶ መሆን እንደሌለበትና ይህ ካልሆነ ግን አሠራሩ ስህተት እንደሚሆን ገልጸዋል።
የአሠሪና ሠራተኛ ደንቦችና መመሪያዎች ሲወጡ በሦስትዮሽ ውይይት እንደሚወሰኑና በአፈጻጸም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችም በዚህ መንገድ እንዲፈቱ እንደሚሠራ ተመልክቷል።
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት ከሰሞኑ በሰጠው ውሳኔ፣ ከልዩ ልዩ ፈቃዶች ውጭ አንድ ሠራተኛ ለ5 ተከታታይ የሥራ ቀናትና ከዚያ በላይ ከሥራ ከቀረ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ መስጠት ሳያስፈልግ የሥራ ውሉን ማቋረጥ እንደሚቻል መግለጹ ይታወሳል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.