#Ethiopia | ታዋቂው ጀርመናዊ የፎቶግራፍ ባለሙያ ደርክ ስኪባ የኢትዮጵያን የስነ ጽሁፍ ባለውለታዎች እና ተተኪ ወጣት ደራሲያንን በካሜራው የቀረጸበት ልዩ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ሊቀርብ ነው።
ይህ ዝግጅት በስንኝ ክርኤቲቭስ እና በጎተ ኢንስቲትዩት ትብብር የተሰናዳ ሲሆን በዶክተር ፌቤን ፋንጮ እና በአሳየኸኝ አስፋው ጥንቅር የቀረበ ነው።
የፊታችን ግንቦት 4 ቀን ከቀኑ 11 ሰዓት ተኩል ጀምሮ በጎተ ኢንስቲትዩት በሚመረቀው በዚህ አውደ ርዕይ ላይ የግጥም ንባብ፣ የሙዚቃ ዝግጅት እና ከደራሲያን ጋር የሚደረጉ ወጎች ይኖራሉ።
በስነ ጽሁፍ እና በኪነ ጥበብ ዙሪያ የተሰባሰቡ እንግዶች የሚገናኙበት እንዲሁም የተለያዩ ምግቦች እና መጠጦች የሚቀርቡበት ልዩ ምሽት ስለሆነ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል።
#culture #literature #photography #art #ethiopianwriters #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa
Source: GetuTemesgen









No comments yet.