ኮዬ ፈጬ የሚገኘው “ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት”

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I የሀገሪቱን ምርጥ አእምሮዎች (Top Scorers) በመሰብሰብ የሚያስተምረው በሸገር ከተማ ኮዬ ፈጬ ክፍለ ከተማ የሚገኘው ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (SIT) በሚዲያ ባለሙያዎች እና በማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ተጎበኘ።

ተቋሙ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ 242 ተማሪዎችን ተቀብሎ በስድስት ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ትምህርት እየሰጠ ይገኛል።

​ከባህላዊው ሴሚስተር በተለየ በዓመት ሦስት “ኳርተሮች” የሚጠቀምበትን ሥርዓት የዘረጋው ኢንስቲትዩቱ፣ የአሜሪካውን በርክሌይ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል የተከተለ ዓለም አቀፍ ካሪኩለም ተግባራዊ አድርጓል። ትምህርቱ የሚሰጠው በሀይብሪድ (በአካልና በቨርቹዋል) ሲሆን፣ በናሳ፣ ጎግል እና ማይክሮሶፍት የሚሰሩ ትውልደ ኢትዮጵያውያንና የውጭ ዜጋ ፕሮፌሰሮች ዋናውን ሌክቸር ይመራሉ።

​ተቋሙ ትኩረት ያደረገባቸው ስድስት ቁልፍ ዘርፎች፦
📌 ​አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)
📌 ​ስፔስ ሳይንስና ኢንጂነሪንግ
📌 ​ኑክሌር ኢንጂነሪንግ
📌 ​ባዮ ቴክኖሎጂ
📌 ​ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግ
📌 ​ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ናቸው።

​የኢንስቲትዩቱ በአራት ዓመት ውስጥ አጠቃላይ የተማሪዎችን ብዛት ከ2,000 እንዳይበልጥ ገድቦ ጥራት ያለው ትምህርት ለመስጠት አቅዷል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: