ታሪካዊ ድል ለኢትዮጵያ! በአማዞን (AWS) የዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ኢትዮጵያዊው ወጣት አሸነፈ!

- Advertisement -
Sidebar AD

🚨🇪🇹🏆

#Ethiopia | ባለፉት ቀናት የዓለምን ትኩረት በሳበውና ከ10,000 በላይ የዓለም ሀገራት ተወዳዳሪዎች በተሳተፉበት የዓለም ትልቁ የአማዞን (Amazon Web Services) የቴክኖሎጂ ውድድር፤ ኢትዮጵያዊው የ24 ዓመቱ ሶፍትዌር መሃንዲስ ናትናኤል ጌጤነው ዘለቀ የዓለም አቀፍ የፈጠራ አሸናፊ (Global Innovation Award) ሆኗል!

ናትናኤል የሰራው “Ivy” የተሰኘው አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ፣ ኢንተርኔት በሌለበት ሁኔታ በሞባይል ስልኮች ላይ እየሰራ ተማሪዎችን የሚያስተምር ዘመን አሻጋሪ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው።

የአማዞን ዋና ኢንጂነሮች የህንድ፣ የአውሮፓ እና የአሜሪካ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋማትን ስራ ወደ ጎን በመተው የናትናኤልን ስራ “የላቀ የቴክኖሎጂ ፈጠራ” በማለት በአንደኛነት መርጠውታል።

ይህ የአማዞን ሽልማት የውድድሩ ማብቂያ ሳይሆን የትልቅ ራዕይ ጅማሮ ነው። ናትናኤል ይህንን ቴክኖሎጂ ወደ ተግባር በመቀየር በመላው አፍሪካ የሚገኙ ተማሪዎችን ተደራሽ ለማድረግ ዝግጅቱን አጠናቋል።

በዚህ ወሳኝ ሳምንት ድምፃችሁን በመስጠት ከጎኑ ለቆማችሁ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ደስ አለን! ኢትዮጵያዊ ፈጠራ በዓለም መድረክ አሸንፏል! 🇪🇹🔥

​#technology #innovation #artificialintelligence #ethiopianexcellence #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2