ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ ይሻላል”

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

አምላክነትን ሲሻ የወደቀ የሰው ልጅን ለማዳን የሰውን ባሕርይ ተዋህዶ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደ፡፡

ከኛ በነሳው ስጋም ወደ ሰማይ አረገ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ይለናል፡፡ “ሔዋንን ዲያብሎስ አሳታት የሞት ምክንያት የሚሆን ቃልን ወለደች፡፡ ድንግል ማርያም ግን መልአክ በአበሠራት ጊዜ ሁሉን ወደ ዘለዓለም ሕይወት የሚመራ አካላዊ ቃልን በሥጋ ወለደች፡፡” በማዳኑ ስራ ውስጥ የቅድስት ድንግል ማርያም ድርሻ ታላቅ ነው፡፡ “የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ፡፡” ሲል ቅዱስ ጳውሎስም ለገላትያ ክርስቲያኖች ጽፏል፡፡ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ 4÷4 ስለፍጹም የሰው ልጆች ፍቅር መድኃኔ ዓለም “በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፣ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳ የታዘዘ ሆነ” ፊልጵ 2÷8 ተብሎ እንደተጻፈ፡፡

“ለቤተ ክርስቲያን ስትል በአደባባይ በጥፊ የተመታህ አቤቱ ይህን ማድረግህ እርስዋን በከበረ ደምህ ትቀድሳት ዘንድ ነው፡፡ ለእርስዋ ሲል ታሥሮ መጎተት የቻለ የበደለውም በደል ሳይኖር፣ ርኩስ ምራቅ ሲተፋበት የታገሠ መድኃኔ ዓለም በእንጨት መስቀል ላይ ተሰቀለ” በማለት የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ቄርሎስ ጌታችንን ገለጸው፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ሰው ሆኖ እንደሚያድነን በመጀመሪያ ለአዳም ቃል ገባለት፡፡ ከዚያም በነቢያት ትንቢት አስነገረ፡፡ በስጋ በተገለጠ ጊዜም የሰቀሉትና የገደሉት አይሁድ ሳይቀሩ እንዲናገሩ አፋቸውን አስከፈታቸው፡፡ አልአዛርን ለአራት ቀናት በመቃብር ከቆየ በኋላ ከሙታን ሲያስነሳው ከአይሁድ ወገን ብዙዎች አመኑ፡፡ አንዳንዶች ግን ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሯቸው፡፡

ወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ በምዕራፍ 11 እንደጻፈው ከጌታችን ተአምራትና ከትምህርቱ የተነሳ ሕዝቡ ሁሉ ትቷቸው እንዳይሔድ የፈሩት አይሁድ ሲማከሩ “በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት የነበረ ቀያፋ የሚሉት ከእነርሱ አንድ፣ እናንተ ምንም አታውቁም፤ ሕዝቡም ሁሉ ከሚጠፋ አንድ ሰው ስለ ሕዝቡ ይሞት ዘንድ እንዲሻለን አታስቡም አላቸው። ይህንም የተናገረ ከራሱ አይደለም፣ ነገር ግን በዚያች ዓመት ሊቀ ካህናት ነበረና ኢየሱስ ስለ ሕዝቡ ሊሞት እንዳለው ትንቢት ተናገረ፡፡ ስለ ሕዝቡም ሁሉ አይደለም÷ ነገር ግን የተበተኑትን የእግዚአብሔርን ልጆች ደግሞ በአንድነት እንዲሰበስባቸው ነው እንጂ።” ተብሎ ተጽፏልና፡፡ በዕለተ ሥቅለተ ክርስቶስ ካሕናት አባቶቻችን የዘጠኝ ሰዓት ስግደት ሲሰገድ “ኦ ዘጥዕመ ሞተ በስጋ” “በስጋው ሞትን የቀመሰ ኢየሱስ ክርስቶስ” እያሉ ልብን በሚያሳዝን ዜማ ያዜማሉ፡፡

በመለኮቱ ሕያው ሲሆን በስጋው ግን ሞትን ቀመሰ፡፡ የአዳምን ሞት በሞቱ ሊሽር መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን በገዛ ፈቃዱ አሳልፎ ሰጠ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለኤፌሶን ክርስቲያኖች ሲጽፍ “ከወደደን ከትልቅ ፍቅሩ የተነሣ በበደላችን ሙታን እንኳ በሆንን ጊዜ ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠን… አስቀድሞ ያዘጋጀውን መልካሙን ሥራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን” ይላል፡፡ የቀድሞው የግብጽ ኦርቶዶክሳውያን ሊቀ ጳጳስ አቡነ “ሺኖዳ እኛ ወደ እርሱ መውጣት ሲያቅተን መድኃኔ ዓለም ወደኛ ወረደ” በማለት ይገልጹታል፡፡ ህዝቡ ሁሉ እንዳይጠፋ ነፍሱን ቤዛ ያደረገውን እርሱን ብለው ዓለምን ትተው የመነኑ ገዳማውያን ጸሎታቸው ኃይልን ያደርጋል። ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና በረከታቸው ያድርብናል።

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: