በአዲስ አበባ በውጭ ሀገር ዜጋ ላይ ስርቆት የፈጸሙ ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ የዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ዜጋን በማዋከብ ስልክ የሰረቁ ሁለት ግለሰቦች፣ በአዲስ አበባ ፖሊስ ፈጣን ክትትል በሰዓታት ልዩነት ውስጥ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጠ።

ድርጊቱ የተፈጸመው ሚያዚያ 23 ቀን 2018 ዓ.ም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1፣ ልዩ ስሙ ኢሰመኮ (ባምቢስ) አካባቢ ነው። ተበዳዩ ኢብራሂም ሀሰን የተባሉ የውጭ ሀገር ዜጋ ከሱፐር ማርኬት ዕቃ ገዝተው ወደ አረፉበት ሐያት ሪጀንሲ ሆቴል በእግራቸው በመጓዝ ላይ ሳሉ ነበር ጥቃቱ የደረሰባቸው።

አብዲ ሀሰን እና ቃልዓብ ወርቁ የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች ግለሰቡን ግራና ቀኝ በመሆን ካዋከቡ በኋላ፣ አንደኛው “ሄድፎን ግዛን” በማለት ትኩረት ሲሰርቅ፤ ሁለተኛው ተጠርጣሪ ግምቱ 200 ሺህ ብር የሚሆን iPhone 15 Pro Max ስልክ ከኪሳቸው ሰርቆ ለመሰወር መሞከሩ ተመልክቷል።

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የባምቢስ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ከአቤቱታው መነሻ በማድረግ ባከናወነው ፈጣን ኦፕሬሽን፣ ሁለቱንም ተጠርጣሪዎች ስልኩን እንደያዙ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

​የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ባስተላለፈው መልእክት፣ በወንጀል ተግባር ራስን ለማበልጸግ የሚሞክሩ አካላት ከህግ ተጠያቂነት እንደማያመልጡ አውቀው ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ እንደሚገባ አሳስቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#መናኸሪያfm ​#AddisAbabaPolice #CrimeNews #Ethiopia #PublicSafety #KirkosSubCity #NewsUpdate


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2