አዲሱ የሞባይል ኔትወርክ አቅራቢ ኩባንያ አስነዋሪ ቪዲዎች እና የግብረሰዶማውያንን ይዘቶች ዘጋለሁ አለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በአሜሪካ የሚገኝ አንድ አዲስ የሞባይል አገልግሎት አቅራቢ ድርጅት፣ ከሥነ-ምግባር ውጪ ናቸው ያላቸውን ይዘቶች የሚዘጋ አገልግሎት ይዞ ብቅ ብሏል።

Radiant Mobile የተሰኘው ይህ ኩባንያ፣ በሀገሪቱ የመጀመሪያው ፖርኖግራፊን እና የLGBT+ ይዘቶችን በኔትወርክ ደረጃ የሚዝጋ የሞባይል ኔትወርክ ለመሆን አልሟል።

​የኩባንያው መስራች የሆኑት ፖል ፊሸር ለኤም.አይ.ቲ ቴክኖሎጂ ሪቪው (MIT Technology Review) ሲናገሩ፦

​”እኛ ከፖርኖግራፊ፣ ከLGBT እና ከትራንስ (Trans) ይዘቶች የጸዳ፣ በኢየሱስ ላይ ያተኮረ አካባቢ የመፍጠር ሙሉ መብት አለን ብለን እናምናለን” ብለዋል።

​ይህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች በስልካቸው ሊያገኟቸው የሚችሉትንና ኩባንያው “ለእምነት የማይመቹ” ያላቸውን ይዘቶች አስቀድሞ የማጣራትና የመከልከል ሥራ ይሰራል።

​Radiant Mobile የራሱ የሆኑ የሞባይል ማማዎች (Cell Towers) የሉትም። ይልቁንም ልክ እንደ ባለፈው ዓመት ሥራ እንደጀመረው የዶናልድ ትራምፕ “Trump Mobile” ሁሉ፣ ከታዋቂው የቴሌኮም ኩባንያ T-Mobile ላይ ባንድዊድዝ (Bandwidth) በመግዛት ለደንበኞቹ የሚያከፋፍል (MVNO) ኩባንያ ሲሆን አገልግሎቱን ባለፈው ማክሰኞ በይፋ ሥራ ጀምሯል።

በኔትወርክ ደረጃ የይዘት ገደብ በማድረግ “ንጹህ” የተባለ የኢንተርኔት ተሞክሮ ለመስጠት መሞከሩ ​በዋናነት ሃይማኖታዊ እሴቶቻቸውን በቴክኖሎጂ አጠቃቀማቸው ላይ ለማንጸባረቅ ለሚፈልጉ ወላጆችና ግለሰቦች ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

​ይህ አዲስ አዝማሚያ በቴክኖሎጂው ዓለም ውስጥ በሃይማኖታዊ እና ፖለቲካዊ አመለካከቶች ላይ የተመሰረቱ “የተለዩ” የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች (Parallel Tech) እያደጉ መምጣታቸውን የሚያሳይ ሌላው ማሳያ ሆኗል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#RadiantMobile #Technology #ChristianTech #JesusCentric #USA #News #MobileNetwork


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: