ከታሪፍ በላይ በሚያስከፍሉ አካላት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ገለጸ
በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ላይ እየታየ ያለውን ሕገ-ወጥ የታሪፍ ጭማሪ ለመቆጣጠር ጥብቅ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቋል፡፡
የሚኒስቴሩ የሕዝብ ግንኙነትና የኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አመለወርቅ ሕዝቅዔል፤ ከተፈቀደው ታሪፍ በላይ ክፍያ የሚጠይቁ አካላት ላይ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የነዳጅ እጥረት በማጋጠሙ ምክንያት በአሽከርካሪዎች የሚደረገውን የታሪፍ ጭማሪ ለመቆጣጠር አስቸጋሪ እንደነበር ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል።
ይሁን እንጂ በአሁኑ ወቅት የነዳጅ አቅርቦት ችግርን ለመቅረፍ መንግሥት በቀን ዘጠኝ ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ወደ ገበያ እንዲቀርብ በማድረጉ፣ በምንም መልኩ በአሽከርካሪዎች የሚደረግ የታሪፍ ጭማሪ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
ይህንን ሕገ-ወጥ ድርጊት ለመከላከልና ሕዝቡ በሕጋዊ ተመን እንዲገለገል ለማድረግ በየደረጃው ከሚገኙ የመንግሥት ተቋማትና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር የተቀናጀ የክትትል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል። በመሆኑም ሕገ-ወጥ ድርጊቱን የሚፈጽሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እያሳሰቡ፣ በድርጊታቸው የሚቀጥሉ ከሆነ ግን የሕግ ተጠያቂነት እንደሚኖርባቸው አስታውቀዋል፡፡
@seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.