ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት የቤት ክፍያ ስርዓቱን አዘመነ!

- Advertisement -
Sidebar AD

#Fastmereja: በሪል እስቴት ዘርፍ በፈጣን የግንባታ ጉዞው የሚታወቀው ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት፣ በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የቤት ክፍያቸውን በህጋዊና ቀልጣፋ መንገድ መፈጸም እንዲችሉ ከቴክኖሎጂ ድርጅቱ ፋስትፔይ (FastPay) ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት በዛሬዉ እለት ተፈራርሟል።

ይህ ስትራቴጂካዊ አጋርነት በዋናነት በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው ውስጥ ኢንቨስት ሲያደርጉ የሚያጋጥማቸውን የገንዘብ ዝውውር እንግልት እና የስጋት መሰናክሎች ለመቅረፍ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ስምምነት ደንበኞች የፋስትፔይን ዲጂታል መድረክ በመጠቀም ከዴማ ሆፕ ሪል እስቴት የሚገዟቸውን የመኖሪያ ቤቶችና የንግድ ሱቆች ክፍያ ባሉበት ሀገር ሆነው በቀላሉ መፈጸም እንደሚችሉ ተገልጿል።

ፋስትፔይ በአሜሪካና በኢትዮጵያ ህጋዊ እውቅና ያለው የክፍያ መንገድ በመሆኑ፣ ዝውውሩ ደህንነቱ የተጠበቀና አስተማማኝ እንደሚሆን የተገለፀ ሲሆን የፋስትፔይ ቴክኖሎዲ ደንበኞት ገበያ ላይ ያለውን ከፍተኛ የገንዘብ ምንዛሬ እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ፣ ዝቅተኛ የአገልግሎት ክፍያ በማስከፈል ገንዘቡ በቀጥታ ወደ ሪል እስቴቱ የባንክ ሂሳብ እንዲገባ እንደሚያደርግ ነዉ የተገለፀዉ።

የፋስትፔይ ኮ-ፋውንደር አቶ ፍፁም መርዳሳ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንደገለጹት፣ ስምምነቱ ለዲያስፖራው ማህበረሰብ ዘመናዊና አስተማማኝ የክፍያ አማራጭን ይዞ መምጣቱን አስረድተዋል።

የዴማ ሆፕ ሪል እስቴት ማርኬቲንግ ማናጀር አቶ ናሆም አለማየሁ በበኩላቸው፣ ድርጅቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምንት የሚጠጉ ፕሮጀክቶችን የጀመረ ሲሆን፣ ግንባታን በፍጥነት በማጠናቀቅና ካርታ ያላቸውን ቤቶች ለደንበኞች በማስረከብ በዘርፉ ተመራጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።

ይህ ሪል እስቴት በሲግናል አካባቢ የሚገኘው “ዴማ ሆፕ ፕራይም” በ18 ወራት ውስጥ 100% ተጠናቆ ለባለቤቶች መተላለፉንና የቦሌ አደይ አበባ ፕሮጀክትም በተመሳሳይ መጠናቀቁን የጠቀሱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የቦሌ ዳውንታውን ፕሮጀክት 90% የደረሰ የግንባታ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በሾላ እና በሌሎች የቦሌ አካባቢዎችም የተለያዩ ሳይቶች በከፍተኛ ፍጥነት በመገንባት ላይ እንደሚገኙ ተመላክቷል ።

ዴማ ሆፕ ሪል እስቴት ከመኖሪያ ቤት ግንባታ ባለፈ “ትውልድ ላይ መስራት ሀገር ላይ መስራት ነው” በሚል መሪ ቃል፣ በመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ የመማሪያ ክፍሎችን በመገንባትና አስፈላጊ ድጋፎችን በማድረግ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ የሚገኝ ድርጅት ነዉ።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2