📌ይህም የተላላፊ በሽታዎችን ተጋላጭነት በእጥፍ ይጨምረዋል ተብሏል።
#Ethiopia | ይህ የተባለው ዓለም አቀፍ የእጅ መታጠብ ቀንን አስመልክቶ የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ባሰናዳው መድረክ ላይ ነው።
በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል የበሽታ መከላከልና ጤና ማበልፀግ ባለሙያ የሆኑት ዶ/ር ሄርጎ አበራ እጅን በአግባቡ መታጠብ በተላላፊ በሽታ የመሞትን ምጣኔ ከ18 በመቶ ወደ 2 በመቶ ይቀንሰዋል ብለዋል።
በኢትዮጵያ እጃቸውን በአግባቡ እና ሳይንሱን ተከትለው የሚታጠቡ የጤና ባለሙያዎች ቁጥር 30 በመቶ ብቻ መሆኑን ዶ/ር ሄርጎ አስረድተዋል።
ከታማሚዎች ፈሳሽ እና መሰል ነገሮች ጋር ንክኪ ያላቸው የጤና ባለሙያዎች ለተላላፊ በሽታዎች የመጋለጥ ዕድላቸው 75 በመቶ በመሆኑ እጃቸውን ሳይንሱ በሚያዘው መልኩ መታጠብ አለባቸው ብለዋል።
#እጅ_መታጠብ የራሱ ቅደም ተከተል እና ሳይንሳዊ አካሄድ አለው ያሉት ዶ/ር ሄርጎ ብዙዎች ግን ይህንን እንደማይገነዘቡ አስረድተዋል።
በጤና ተቋማት፣ በምግብ ቤቶችና የሥራ ቦታዎች ንፁህ ውሃ፣ ሳሙናና የመታጠቢያ አልኮል በማቅረብ ሰዎች እጃቸውን እንዲታጠቡ የማበረታታት ልምድ ደካማ መሆኑንም ዶ/ር ሄርጎ አበራ አንስተዋል።
ብዙ ምግብ ቤቶች አንድ ሳሙና ለብዙ ሰው ያስቀምጣሉ፣ይህ የበሽታ አምጪ ጀርሞች መከማቻ እንጂ የንፅህና መጠበቂያ መንገድ እንዳልሆነም አስረድተዋል።
በዓለም የጤና ድርጅት ከ2009 ጀምሮ የእጅ መታጠብ ቀን ዘንድሮ ለ17ኛ ጊዜ የተከበረ ሲሆን በጤና ሚንስትር የኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከዓለም ጤና ድርጅት፣ ጤና ሚንስትር ከሌሎች ተቋማት ተጠሪዎች በተገኙበት በፖናል ውይይት ተከብሯል።
እጅን መታጠብ በንክኪ፣ በአየርና በፈሳሽ ተላላፊ በሽታዎችን 50 በመቶ፣ መድሃኒት የተላመዱ በሽታዎችን ደግሞ 70 በመቶ ይቀንሳልና እጃችሁን በየጊዜው በአግባቡ ታጠቡ ተብላችኋል።
Via Sheger Fm
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen








No comments yet.