ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ግንዛቤ ለማሳደግ የመራቢያ አካሉን በመጠቀም የፖሊስ መኪና የጎተተዉ ግለሰብ መነጋገሪያ ሆኗልጠንካራዉ ሰው…

- Advertisement -
Sidebar AD
ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ግንዛቤ ለማሳደግ የመራቢያ አካሉን በመጠቀም የፖሊስ መኪና የጎተተዉ ግለሰብ መነጋገሪያ ሆኗል
ጠንካራዉ ሰው በአለም ላይ በብልቱ መኪና ለመጎተት የመጀመሪያው ሰው ሆኗል የተባለ ሲሆን ዓላማዉን ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ግንዛቤን ለማሳደግ የተደረገ እንደሆነ ተናግሯል።
የ50 አመቱ ጆን ስቴፈን ወንድነቱን ተጠቅሞ ባለ 2 ቶን የፈረንሳይ ፖሊስ መኪና 131 ጫማ ያህል በመኖሪያ ጎዳና ላይ ጎትቷል። ይህዉ ተግባር በምዕራብ ዮርክሻየር፣ እንግሊዝ ውስጥ የተከናወነ ሲሆን ግራ የተጋቡ ነዋሪዎች ሲመለከቱ የነበረውን አስገራሚ ፈተና አጠናቋል።
የማርሻል አርት ኤክስፐርቱ የወንዶች የጤና ጉዳዮችን ግንዛቤ ለማሳደግ በሚል አነጋጋሪ አጀንዳን ለማጣመር መወሰኑን ገልጿል፡፡”አልዋሽም፤ ትንሽ ጎድቶኛል” ነገር ግን አእምሮዬ አተኩሮ ነበር እናም ወደ 40 ሜትሮች ተሸከርካሪዉን ጎትቼዋለሁኝ ማለቱን ዳጉ ጆርናል ዘግባል።
የፕሮስቴት ካንሰር በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በወንዶች ላይ በጣም የተለመደ ካንሰር ነው፡፡ ለወንዶች በካንሰር ረገድ ሁለተኛዉ የሞት ምክንያት ነው። ከ 6 ወንዶች መካከል አንዱ በህይወት ዘመኑ የፕሮስቴት ካንሰር ምርመራ እና ህክምና ሂደት ዉስጥ ያልፋል፡፡
በኤደን ሽመልስ
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: