አቶ ዳውድ ኢብሳ በጸጥታ ስጋት ምክንያት በምርጫ እንዳይወዳደሩ ኦነግ ወሰነ

- Advertisement -
Sidebar AD

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ለመወዳደር ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በሚወዳደሩበት የምርጫ ወረዳ ባለው የጸጥታ ስጋት ምክንያት ከውድድሩ እንዲወጡ ፓርቲው መወሰኑን ለአሐዱ አስታውቋል።

የኦነግ የስነ ምግባር እና ቁጥጥር ኮሚቴ ሊቀ መንበር አቶ አለማየሁ ዲሮ ለአሐዱ እንደገለጹት አቶ ዳውድ የሚወዳደሩበት አካባቢ የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ ባለመሆኑ ከምርጫው ፉክክሩ እንዲወጡ ድርጅቱ ወስኗል ብለዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ለምርጫ ቦርድ 163 ዕጩዎችን አቅርቦ የነበረ ሲሆን ምርጫ ቦርድ 128 ዕጩዎችን ማጽደቁን ተከትሎ ፓርቲው በ128 የምርጫ ወረዳዎች እንደሚወዳደር አቶ አለማየሁ ገልጸዋል።

ኦነግ ለምርጫው ካቀረባቸው ዕጩዎች መካከል ገሚሶቹ ለፌደራል ምክር ቤት የሚወዳደሩ ሲሆን ፓርቲው ለኦሮሚያ ክልል ካቀረባቸው ዕጩዎች በተጨማሪ በአዲስ አበባ ፣ በድሬዳዋ ፣ በሐረሪ ክልል ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በአማራ ክልል ከሚሴ አካባቢ እንደሚወዳደር ተገልጿል።

#አሐዱ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2