#Ethiopia | የማንችስተር ዩናይትዱ የዝግጅት ክፍል ውጤት የሆነው ወጣቱ ድንቅ ታላንት ኮቢ ማይኖ፣ በ35ኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ተብሎ ተመርጧል።
ማይኖ በተለይ በታሪካዊው ተቀናቃኝ ሊቨርፑል ላይ ያስቆጠራት ያቺ አስደናቂ የማሸነፊያ ግብ፣ ለዚህ ክብር ለመታጨትና ሽልማቱን ለመውሰድ ዋነኛ ምክንያት ሆናለታል።
እድሜው ገና ወጣት ቢሆንም፣ በሜዳ ላይ የሚያሳየው መረጋጋትና ብስለት የብዙዎችን ቀልብ መሳቡን ቀጥሏል።
ምንም እንኳን የቡድኑ የውድድር ዘመን ጉዞ ውጣ ውረድ የበዛበት ቢሆንም፣ የተጨዋቾቹ የግል ብቃት ግን እጅግ አስደናቂ ነው። ዘንድሮ የክለቡ ተጨዋቾች የሳምንቱን ምርጥ ተጨዋች ሽልማት የግላቸው በማድረግ ረገድ ወደር አልተገኘላቸውም፦
13/36፡ በዘንድሮው የውድድር ዘመን እስካሁን ከተሰጡት 36 የሳምንቱ ምርጥ ተጨዋች ሽልማቶች መካከል 13ቱን የወሰዱት የኦልድትራፎርድ ተጨዋቾች ናቸው።
ይህም ማለት በሊጉ ካሉት የሳምንቱ ኮከብ ሽልማቶች ውስጥ 36% የሚሆነውን ማንችስተር ዩናይትድ ጠቅልሎ ወስዷል ማለት ነው።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#KobbieMainoo #MUFC #PremierLeague #ManUnited #Ethiopia #FootballNews #የሳምንቱ_ኮከብ
Source: GetuTemesgen









No comments yet.