የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዓለም አቀፍ ዕውቅና ተቸረው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ላይ ባከናወነው የዲጂታል ሪፎርም በ2025 የኢ.አር.ፒ ዓለም አቀፍ ሽልማት ሥነ ሥርዓት ላይ የዓመቱ ምርጥ የትራንስፎርሜሽን ፕሮጀክት አሸናፊ ሆኗል።

ፕሮጀክት ስማይል የተሰኘውና በዘመናዊ የሳፕ ቴክኖሎጂ የታገዘው ይህ አሰራር ቀደም ሲል የነበረውን በእጅ የሚከናወን የተበጣጠሰ አሰራር በማስቀረት የግዥ፣ የመጋዘን፣ የፋይናንስና የስርጭት ስራዎችን በአንድ ማዕከል ማስተሳሰር ችሏል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብዱልቀድር ገልገሎ እንደገለጹት ተቋሙ የዲጂታል ሪፎርም ካከናወነ በኋላ የሥራ አፈጻጸሙ እጅግ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል።

ከአምስት ዓመታት በፊት ዓመታዊ የግዥ መጠኑ 3 ቢሊዮን ብር ብቻ የነበረ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ለጤና ተቋማት የቀረቡ መድኃኒቶች የሽያጭ መጠን 11.5 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

ይህም በግዥ ዝግጅት ላይ ያሉ ምርቶችን ሳይጨምር የተመዘገበ ስኬት መሆኑ ተመልክቷል።

አዲሱ የተቀናጀ የዲጂታል ሥርዓት ሀገር አቀፍ የመድኃኒት ፍላጎትን በግልጽ ለመለየት ያስቻለ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ አጠቃላይ የመድኃኒት ፍላጎት 24 ቢሊዮን ብር መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል።

በግሎባል ፈንድ የገንዘብ ድጋፍ የተተገበረው ይህ ፕሮጀክት የመድኃኒት ብክነትን በመቀነስና የፍላጎት ትንበያ ጥራትን በማሻሻል ረገድ ውጤታማ መሆኑ ተረጋግጧል።

ይህ ስኬት ኢትዮጵያ በ2030 የዲጂታል ስትራቴጂን እውን ለማድረግ ለምታደርገው ጥረት የመንግሥት ተቋማት በቴክኖሎጂ መዘመናቸው ያለውን ፋይዳ በግልጽ ያሳየ ተደርጎ ተወስዷል።

#ጤና #ዲጂታልሪፎርም #የመድኃኒትአቅርቦት #ቴክኖሎጂ #ሽልማት
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: