በሺህዎች የሚቆጠሩ የንግድ እና የነዳጅ ጫኝ መርከቦች በኢራን ፍኖተ-ሆርሙዝ እንዳያልፉ እገዳ ተጥሎባቸው መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው የነዳጅ እጥረቱ በየቦታው እየተስፋፋ ዋጋውም እየናረ መምጣቱ እየተገለጸ ነው ። በኢራን ክልከላ የተነሳ 22,500 መርከበኞች በ1,550 የንግድ መርከቦች ውስጥ በባሕረ መስመሩ ማለፍ ሳይችሉ መቅረታቸው ከሰሞኑ ተዘግቧል ። የነዳጅ እጥረት ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች እክሎችን እየፈጠረ መሆኑን የተለያዩ ሰዎች በምሬት እየተናገሩ ነው ።
በናፍጣ እጥረት ምክንያት እየናረ በመጣው የጭነት መጓጓዣ ዋጋ የተነሳ የሙዝ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቸገራቸውን ለዶይቸ ቬለ (DW) የተናገሩ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጋሞ ዞን ሙዝ አምራች አርሶአደሮችን መጥቀስ ይቻላል ። አርሶ አደሮቹ እንዳሉት፦ ቀደም ሲል ከ40 እስከ 50 ሺህ ብር ይጫን ነበረው አንድ አይሱዚ የጭነት ተሸርካሪ በአሁኑ ወቅት በአራት እጥፍ በመጨመሩ ምርታቸውን ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ተቸግረዋል ። የአርባምንጭ ከተማ አስተዳዳር ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ በበኩሉ በናፍጣ አቅርቦት ላይ የሚካሄደውን ማጭበርበር ለመከላከል የኩፖን አሠራር መጀመሩን ዐሳውቋል ።
DW Amharic
Source: Yeneta Tube









No comments yet.