እስክርቢቶን በማስመሰል የትንባሆ ምርቶች ወደ ገበያ እየቀረቡ መሆኑ ተገለፀ

- Advertisement -
Sidebar AD

እስክርቢቶን ጨምሮ የተለያዩ የማያስጠረጥሩና የተመሳሰሉ መንገዶችን በመጠቀም የትንባሆ ምርቶች ወደ ገበያ እየገቡ መሆኑን የኢትዮጵያ ምግብና መድሀኒት ባለስልጣን አስታውቋል።

የትንባሆ ኢንደስትሪው አሁን ላይ በተለያየ መንገድ ምርቶችን እያመረቱ መሆኑን የገለፁት የባለስልጣኑ የዘርፉ ቁጥጥር ዴስክ ኃላፊ አቶ ቶሎሳ ገመዳ አይነታቸውን በመቀየር ወደ ገበያ እየገቡ እና እየተመረቱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በብዛት በሚጨስ መልኩ ከነበሩት የሲጋራ አይነቶች በተለየ መልኩ የኤሌክትሮኒክ ሲጋራ ምርቶች መምጣታቸውን አስታውሰዋል፡፡

ይህንንም ብዙ ሰው የማያቀው በመሆኑ እንደ ካፌና ሬስቶራንት በመሳሰሉ ትምባሆ እንዳይጨስባቸው በተከለከሉ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ መድሀኒት የሚወስዱና በማስመስል እንደሚጠቀሙበት ገልፀዋል።

ይህ እንቅስቃሴ ወጣቶች በብዛት በሚገኙበት አካባቢዎች ላይ የሚካሄድ መሆኑን አንስተዋል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ እንደዚህ መሰል ድርጊቶችን ሲመለከት ጥቆማ በመስጠት መተባበር እንዳለበት ያሳሰቡ ሲሆን ተቋሙ በበኩሉ ይህንን አሰራር በማጋለጥና ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፈጠር ወጣቶችን ከዚህ አደገኛ ምርት ለመጠበቅ በስፋት እየሰራበት መሆኑን ተናግረዋል።

#አሐዱ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: