የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው ቦታዎች የትኞቹ እንደሆኑ ያውቃሉ?
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የምርጫ ቅስቀሳ ሥነ ምግባር መመሪያ ቁጥር 33/2018 አንቀጽ 11 መሰረት የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከለባቸው ቦታዎች እና ሁኔታዎች የሚከተሉት ናቸው፦
1) በሚከተሉት ቦታዎች የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግም ሆነ የምርጫ ቅስቀሳ ጥሪ ማድረጊያ ቁሳቁሶችን መለጠፍ፣ ማስቀመጥ ወይም በማንኛውም መንገድ ማስራጨት የተከለከለ ነው።
ሀ) ቤተ ክርስትያኖች፤
ለ) መስጊዶች፣
ሐ) ወታደራዊ ካምፖች እና ፖሊስ ጣቢያዎች፤
መ) በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ፅ/ቤቶች አካባቢ
ሠ) የመማር ማስተማር ሂደት ተግባር እየተከናወነ በሚገኝበት ወቅት በትምህርት ቤቶች እና በትምህርት ቤቶች አካባቢ በ200 መቶ ሜትር ርቀት ዙሪያ፤
ረ) ህዝብ የዕለት ተእለት ግብይት በሚፈዕምባቸው እና በተወሰኑ ቀናት በገጠርም ሆነ በከተማ በይፋ ገበያ እየተካሄደ በሚገኝባቸው ቦታዎች በ200 መቶ ሜትር ዙሪያ ከልል፤
ሰ) በቦርዱ ጽ/ቤት፣ በምርጫ ጣቢያ ጽ/ቤት፣ በምርጫ ከልል ጽ/ቤት እና የክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በ200 መቶ ሜትር ዙሪያ ክልል፤
ሸ) ሌላ ቀድሞ የተጀመረ ህዝባዊ ስብሰባ ወይም የምረጡኝ ቅስቀሳ እየተካሄደ ባለበት ቦታ።
2) በዚህ አንቀጽ በንኡስ አንቀጽ (1) ላይ የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ ከተከለከሉ ቦታዎች ውጪ በሆነ ቦታ የሚደረግ የምርጫ ቅስቀሳ የተከለከሉ ቦታዎች ላይ የሚደረገውን እንቅስቃሴ የማያደናቅፍ መሆን አለበት።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.